#FastMereja I በ1999 “አላማሽም” በ2003 “ተገርሜ” በ2011 “እንነጋገር” በተሰኙት የሙዚቃ አልበሞቹ በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትና ተቀባይነት ያገኘው የድምፃዊ አቤል ሙሉጌታ 4ኛው “ቅን” የተሰኘው አልበሙ 14 ትራኮችን የያዘ ሲሆን ስራውን ሰርቶ ለማጠናቀቅም 5 ዓመታትን ወስዷል፡፡
የሁሉም ትራኮች ግጥምና ዜማ በራሱ በድምፃዊው በአቤል ሙሉጌታ ሲሰሩ በቅንብር ካሙዙ ካሳ፣ አቤል ጳውሎስ፣ ታምሩ አማረ፣ አዲስ ፍቃዱ፣ ሮቤል እንዳለ፣ አብርሃም ኪዳኔና ሙሳ ማቲ በሚከሲንግ ሰለምን ሃ/ማርያም፣ አቤል ጳውሎስና አብርሃም ኪዳኔ በማስተሪንግ ኪሩቤል ተስፋዬ ተሳትፈውበታል።
ቅን አልበም የሀገራዊ፣ የማህበራዊ፣ የፍቅር፣ የፍልስፍናና ታሪካዊ ጉዳዮችን የሚያነሳ ሲሆን የሙዚቃ አልበሙ ዛሬ አርብ ሐምሌ 11/2017 ዓ.ም ለአድማጮች በራሱ የአቤል ሙሉጌታ የዩቲዩብ ቻናል ይለቀቃል።
አቤል ሙሉጌታ ለበርካታ የሀገራችን አንጋፋና ወጣት ድምፃዊያን ማለትም ለፀሃዬ ዮሃንስ፣ ለዳዊት ፅጌ፣ ለብዙአየሁ ደምሴ፣ ለሄለን በርሄ፤ ለቬሮኒካ አዳነ፣ ለራሄል ጌቱ፣ ለተመስገን ገ/እግዚአብሔር፣ ለመስፍን (ነይ በክረምት)ን ጨምሮ ለሌሎች በርካታ ድምፃውያን ተወዳጅ የሆኑ የግጥምና ዜማ ስራዎችን ሰርቷል።
#ኪነ_ጥበብ





1 comment
ማን ሊሰማ 🤣🤣🤣🤣