banner

በሀረር ከተማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰው አካልና ንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

#FastMereja I በሀረር ከተማ አራተኛ መንገድ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ በሰው አካልና በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ የሀረሪ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

በኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር ጣሰው ቻለው እንደገለፁት አራተኛ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በደረሰው የትራፊክ በአጠቃላይ በ8 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልፀው ከእነኚህ መካከልም በ4 ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት እንዲሁም በ4 ሰዎች ላይ ቀላል ጉዳት ደርሷል።

የደረሰው አደጋ መንስኤ ፍሬን የበጠሰ ውሃ የጫነ ቦቴ ተሽከርካሪ በመንገዱ ላይ ሲጓዙ የነበሩ 3 ተሽከርካሪዎችን በመግጨት ጉዳት እንዲከሰት ማድረጉን ተናግረዋል።




2 comments

Tesfa Adane July 18, 2025 - 5:48 pm

እግዚኦ መሃረነ ክርስቶስ

Reply
ጉን ዳን July 18, 2025 - 5:49 pm

ኮሪደር ላይስ እሱም ሊነገርን ይገባል እንደ ንብረትና ሰው

Reply

Leave a Comment