banner

ፓስተር ትዝታው ሳሙኤል ቅሬታ ቀረበበት

#FastMereja I ባሳለፍነው እሁድ በሚሊኒየም አዳራሽ “ለኢየሱስ” የተሰኘ የመዝሙር ድግስ ተዘጋጅቶ ነበር፣ በዝግጅቱ ላይ የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ታድመው የነበረ ሲሆን በመድረኩ ላይ ሲቀርቡ የነበሩ ትዕይንቶች የመበሻሸቅ ነገሮች በመግባቱ ቅሬታ እንደፈጠረባቸው ታዳሚዎቹ ገልጿል።

እኛ የታደምነው ለአምልኮ እንጂ ለብሽሽቅ አይደለም ያሉት ታዳሚዎቹ “ወንጌል ፍቅር እንጂ ብሽሽቅ አይደለም” ሲሉ ቅሬታቸውን አሰምቷል።

አኩ የተባለ የእምነቱ ተከታይ የታዘበውን እንደዚህ ብሏል “የእነ ፓስተር ትዝታው፣ በጋሻውና ዘማሪት ዘርፌከበደ በተመለከተ ወደ ወንጌል ብርሃን መምጣት ያስደሰተኝን ያህል ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በማስተውለው ቀድሞ የተማሩና ያስተማሩባትን ቤተክርስቲያን ያገለገሉትን ህዝብ የማብሸቅ የመሳደብ የማንቋሸሽ ስራ እውን እነዚህ ሰዎች እውነት ገብቷቸው ወይስ የግል ፀብ ገጥሟቸው ነው ወደ እኛ ማህበር የተቀላቀሉት ብዬ እንድጠይቅ አድርጎኛል።” ሲል የታዘበውን ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮችም በፓስተር ትዝታው ላይ ያላቸውን ቅሬታ በተለያየ መንገድ ሲገልጹ ታይቷል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓስተር ትዝታው ሳሙኤል ወደ ኢትዮጵያ መግባቱን ተከትሎ ክስ መመስረቷ አይዘነጋም።

Leave a Comment