banner

ጄቱር ኢትዮጵያ እና ሱዌይስ ሞተርስ ዘላቂ አረንጓዴ አሻራ ለመተው የአረንጓዴውን ሌጋሲ አላማ መቀላቀላቸወወን ገለጹ

#FastMereja – ጄቱር ኢትዮጵያ እና ሱዌይስ ሞተርስ ጋር በመተባበር በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የአረንጓዴው አሻራ ዘመቻ የአየር ንብረት ለውጥን ለመዋጋት፣ የተፈጥሮ አካባቢን ወደነበረበት ለመመለስ እና ለመጪዎቹ ትውልዶች ጤናማ እና አረንጓዴ ሀገርን ለማስተላለፍ የሚደረገ እንቅስቃሴ ነዉ ተብሏል።

እንደ የድርጅታችን ማህበራዊ ሀላፊነት ጄቱር ኢትዮጵያ እና ሱዌይስ ሞተርስ በዚህ ጅምር በመሳተፍ ኩራት ይሰማናል። ዛፎችን በመትከል፣ ሌሎች ትርጉም ያለው እርምጃ እንዲወስዱ በማነሳሳት ለአካባቢ ጥበቃ ዘላቂነት የበኩላችንን አስተዋጽኦ ለማድረግ ዓላማ እናደርጋለን ብሏል።

“ጄቱር ኢትዮጵያ እና ሱዌይስ ሞተርስ እውነተኛ እድገት የሚለካው በፈጠራና በማደግ ብቻ ሳይሆን በተውነው መልካም ትሩፋት ነው ብለን እናምናለን። ዛሬ ዛፎችን ብቻ ሳይሆን ተስፋን፣ ጽናትን እና የኢትዮጵያን የወደፊት እጣ ፈንታ ተክተናል” ሲል ኩባንያው ኃላፊዎች ተናግሯል።

ጄቱር ኢትዮጵያ እና ሱዌይስ ሞተርስ በጋራ በመሆን ለውጥን ለማምጣት፣ አካባቢን ለመንከባከብ እና ጠቃሚ የሆነ ትሩፋትን ለመተው ቆርጠው መነሳታቸውን ገልጿል።

#ማህበራዊ





Leave a Comment