#FastMereja I የባቡል ኸይር በጎ አድራጎት ድርጅት የምንጊዜም አጋርና አምባሳደር ወጣቱ ባለጸጋ ምረትአብ ሙሉጌታ እና የአፍሮ ሊንክ ግሩፕ ባለቤት አቶ ሚኪያስ አያሌው በዛሬው ዕለት መስከረም 1/2018 ዓ/ም የዘመን መለወጫ በዓልን ባቡል ኸይር ድርጅት ምሳ በማብላት እና ድጋፍ በማድረግ በአልን ከምስኪን ወገኖቻችን ጋር አሳለፉ።
አቶ ሚኪያስ አያሌው 5 ሺ ለሚሆኑ ወገኖች ሙሉ የምሳ ወጪ በመሸፈን ምሳ ያበላ ሲሆን ምረትአብ ሙልጌታ ደግሞ የ500 ሺ ብር ድጋፍ አድርጓል።
ሁለቱ ባለጸጋዎች በዓልን ከምስኪናን ጋር ማሳለፋችን እጅግ ደስታ ሰጥቶናል እኛ ኢትዮጵያዊያኖች እርስ በእርሳችን መረዳዳትና መደጋገፍ አለብን ባቡልኸይር እየሰራው ያለው በጎ ተግባር እጅግ የሚያሥደስትና የሚያኮራ ስለሆነ ሁላችንም በትርፍ ጊዜያችን በባቡልኸይር እየተገኘን ከምስኪን ወገኖቻችን ጋር እያሳለፍን ተዝቆ የማያልቀውን የእናቶችን እና የአባቶችን ምረቃ ተቀብለን ልንባረክ ይገባል ብለዋል።
የባቡልኸይር በጎ አድራጎት መስራች ከሆኑት መካከል አንዷ የሆነችው ወይዘሮ ፈትያ መሐመድ የምንጊዜም ደጋፊያችን ሚኪና ምረትአብ በዛሬው ዕለት በአልን ከቤተሰቦቻችሁ ጋር ማሳለፍ እየቻላችሁ አስታዋሽ የሌላቸው እናቶቻችን እና አባቶቻችን ይበልጡብናል ብላችሁ ምሳ አብልታችሁ የ 500 ሺ ብር ድጋፍ አድርጋችሁ አብራችሁን ስለዋላችሁ ፈጣሪ በወጣ ይተካላችሁ በረካ ሁኑልን እጅግ አድርገን እናመሠግናችኋለን በማለት ምስጋናዋን ገልጻለች።
#ማህበራዊ




