0
#FastMereja | የጅዳው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት ላለፉት 13 ዓመታት ደመወዟን ያላገኘች አንዲት ዜጋ ሀቋን እንድታገኝ አስችሏል!
ወ/ት ዘምዘም ቱኒ እሰሞ የተባሉ ኢትዮጵያዊት ዜጋ በህጋዊ መንገድ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ተቡክ ከተማ ከገቡ በኋላ በአጠቃላይ 14 ዓመታትን ሰርተዋል።
ሆኖም፣ ከዚህ ውስጥ የ13 ዓመታት ደመወዝ ሳይከፈላቸው በመቆየቱ ለቆንስላ ጽ/ቤቱ የድጋፍ ጥያቄ አቅርበው ነበር።
ቆንስላ ጽ/ቤቱ ጉዳዩን በንቃት በመከታተል ባደረገው ከፍተኛ ጥረት፣ ዜግቷ ያልተከፈላቸው ቀሪ የ13 ዓመት ደመወዝ በድምሩ 109,000 (አንድ መቶ ዘጠኝ ሺህ የሳዑዲ ሪያል) ሙሉ በሙሉ እንዲከፈላቸው ማድረግ ተችሏል!
ገንዘቡ ከተከፈላቸው በኋላም ወ/ት ዘምዘም የጉዞ ሰነድ ተዘጋጅቶላቸው በሰላም ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሯል። ዜግቷም ለተደረገላቸው ድጋፍ ለቆንስላ ጽ/ቤቱ ልባዊ ምስጋና አቅርበዋል።
ማሳሰቢያ፡ ቆንስላ ጽ/ቤቱ በዚህ አጋጣሚ ለስራ ወደ የትኛውም አገር የሚደረጉ ጉዞዎች ህጋዊ መንገድን ብቻ እንዲከተሉ ለዜጎች ጥብቅ ጥሪ አቅርቧል።
Via የጅዳው የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት

1 comment
ሆሎ ውዴ ከአንች አርግዣለሁ