#FastMereja I ስፓይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ መከላከል ላይ ያተኮረ ሀገርአቀፍ ኮንፈረንስ በዛሬዉ እለት ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም ተከበረ።
አሊያንስ ፎር በርዝ ድፌክት (አብዲ) ከሪች አናዘር ፋውንዴሽን፣ ከግሎባል አልያንስ ፎርኢምፕሩቪድ ኒውትሪሽን(GAIN) ከባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ እና ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የነርቭ ዘንግ ከፍተት እና ሀይድሮሴፋለስን መከላከል የሚያስችል በኢትዮጵያ ምግብን በፎሊክ አሲድ ማበልፀግ ላይ ያተኮረ ኮንፈረንስ በዛሬዉ እለት አካሂዷል።
ስፒና ቢፊዳ የአከርካሪ አጥንት እና የነርቭ ዘንግ በትክክል ሳይፈጠሩ ሲቀሩ የሚከሰት ከባድ ከአፈጣጠር ጋር ተያይዞ የሚከሰት ችግር እንደሆነ እና የአካል እና የግንዛቤ ችግሮችን ጨምሮ የዕድሜ ልክ አካል ጉዳተኝነትን ሊያስከትል የሚችል የጤና ችግር መሆኑ ተገለፀ።
በሽታው በሺዎች የሚቆጠሩ ህጻናትን በየዓመቱ እያጠቃ የሚገኝ እንደሆነ እና ቅድመ መከላከል በችግሩ ለተጎዱ ግለሰቦች እና ቤተሰቦቻቸው የጤና ውጤቶችን እና የህይወት ጥራትን ለማሻሻል ወሳኝ መሆኑ በዛሬዉ መርሀ ግብር ተገልጿል።
ኮንፈረንሱ መሪዎችን፥ ፖሊሲ አውጪዎችን እና አጋሮችን በመጥራት ኢትዮጵያ የነርቭ ዘንግ ከፍተትን ለመከላከል እና ቀጣይነት ያለው መጠነ ሰፊ የምግብ ማበልጸግ ጅምርን ለማሳደግ ያለዉን ቁርጠኝነት በመድረኩ ገልጿል።
ይህ ኮንፈረንስ ለሁለት ቀናት ማለትም ከጥቅምት 10-11 ቀን 2018ዓ.ም በAYA አዲስ ሆቴል የተካሄደ ሲሆን “አከስለሬት አክሽን ፎር ስፒና ቢፊዳ እና ሀይድሮሴፋለስ” በሚል መሪ ቃል የአለም አቀፍ ስፓይና ቢፊዳ እና ሀይድሮሲፋለስ ቀንን አስመልከቶ ነዉ እየተከበረ የሚገኘዉ።
ምግብን በፎሊክ አሲድ ማበልፀግ የአከርካሪ አጥንት እና ሌሎች የነርቭ ዘንግ እንዲሁም የአፈጣጠር ችግሮችን ለመቀነስ የተረጋገጠ ሳይንሳዊ ስልት ነው። ዋና ዋና ምግቦችን በተለይም የስንዴ ዱቄት፣ ዘይት እንዲሁም የምግብ ጨዉን በ ፎሊከ አሲድ በማበልጸግ የነዚህን የአፈጣጠር ችግሮችን በእጅጉ እንደሚቀንስ ነዉ የተገለፀዉ።
በመርሀ ግብሩ የተመጣጠነ ምግብ አስፈላጊነት እንዲሁም ስለ ስነ-ምግብ እና ስለ ሥነ ተዋልዶ ጤና ግንዛቤ ይሰጥበታልም ተብሏል።




