banner

የኢትዮጵያን የስራ እና የንግድ አኗኗር የሚያሻሽል ቴክኖሎጂ ይፋ ተደረገ

#FastMereja I ማርቭርልስ ክሬቲቭ ቴክኖሎጂ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለውን የሥራ እና የንግድ አኗኗር ዘመናዊ ለማድረግ የተዘጋጁ ሁለት ታላላቅ ዲጂታል መድረኮች መላ ጆብስ (Mela Jobs) እና መላ ገበያ (Mela Gebeya) ቴክኖሎጂን በዛሬዉ እለት ጥቅምት 18/2018 ዓ.ም በይፋ ተጀምሯል።

በሦስት ሥራ ፈጣሪዎች የተመሰረተው Marvels Creative Technology በኢትዮጵያ ተደራሽነትን እና ዲጂታል ዕድገትን የሚያሻሽሉ ፈጠራ ያላቸው መላ ገበያ እና መላ ጆብስ ነዉ ይፋ ያረጉት።

መላ ጆብስ ከመሠረታዊ የሥራ ማስታወቂያዎች የዘለለ ተጠቃሚዎች ለቀጣሪዎች ጎልተው እንዲታዩ የሚያስችላቸውን፣ ለሀገር ውስጥም ሆነ ለዓለም አቀፍ መስፈርቶች የሚስማማ ሙያዊ የሥራ ልምድ (CV) በራስ-ስር የሚያዘጋጅ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የተደገፈ የሲቪ ማዘጋጃ ያለዉ ቴክኖሎጂ ነዉ።

መላ ገበያ ቀላልነትን፣ መተማመንን እና ቴክኖሎጂን በአንድ ዲጂታል የገበያ ቦታ በማጣመር ኢትዮጵያውያን ምርቶችን በመስመር ላይ የሚገዙበትን እና የሚሸጡበትን መንገድ የዘረጋ ሲሆን በመላ ገበያ፣ ተጠቃሚዎች ሰፊ ዓይነት ምርቶችን ከሀገር ውስጥ የእጅ ሥራዎች እና የፋሽን ዕቃዎች እስከ ኤሌክትሮኒክስ ከተረጋገጡ ሻጮች ማግኘት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል።

ይህ ቴክኖሎጂ የኢትዮጵያ ሻጮች ምርቶቻቸውን ለሰፊው ሕዝብ እንዲያቀርቡ የሚያስችላቸውን መሣሪያዎችን በመስጠት ማብቃት ላይ ሲሆን ይህም ሻጮች ብክነትን እንዲያስወግዱ እና ሥራቸውን ቀልጣፋ እንዲያደርጉ የሚያግዝ ሲሆን የዚህ ቴክኖሎጂ ዓላማ በመስመር ላይ መገበያየትን ቀላል ማድረግ ብቻ ሳይሆን አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በመደገፍ የኢትዮጵያን ዲጂታል ኢኮኖሚ ማጠናከር ጭምር እንደሆነ ተገልጿል።





Leave a Comment