#FastMereja I ዓለም አቀፍ እውቅና ያላቸው የጆቱን የኢፖክሲ እና የወለል ቀለሞችን ለገበያው ለማቅረብ የማስተዋወቂያ ፕሮግራሙ ጥቅምት 20 እና ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም አዲስ በተከፈተው ሾው ሩም ተከናወነ። በፕሮግራሙ ላይ በዘርፉ የተሰማሩ የድርጅት ተወካዮች ተገኝቷል።
የጆቱን የወለል ቀለሞችን በኢትዮጵያ ለማከፋፈል ፍቃድ ወስዶ ስራ የጀመረው ካሙር ሞደርን ሊቪንግ ሲሆን
ወ/ሮ ሙና ያሲን የካሙር ሞደርን ሊቪንግ ዋና ስራ አስኪያጅ በመድረኩ ባደረጉት ንግግር ካሙር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣውን ከፍተኛ ጥራት ያላቸውን የግንባታ ማጠናቀቂያ ቁሳቁሶች ፍላጎት ለማሟላት አላማ አድርገን እየደራን እንገኛለን ብሏል።
ይህ ራዕይ ወደ ተግባር ተቀይሮ የሚያምሩ ቦታዎችን መፍጠር፣ የአካባቢውን የግንባታ ኢንዱስትሪ መደገፍ እና በገበያ ውስጥ የጥራት እና የንድፍ ደረጃዎችን ለማሳደግ እንዲሁም በፈጠራ፣ በጥራት እና በአስተማማኝነቱ በአለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ስም ጆቱን ከካሙር ጋር ተመሳሳይ እሴቶችን በመጋራቱ አንድ ላይ ሆነን ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የጌጣጌጥ ቀለሞችን ብቻ ሳይሆን በማንኛውም አካባቢ ውስጥ ያሉ መዋቅሮችን ለመጠበቅ እና ለማሻሻል የተነደፉ የላቁ የመከላከያ ሽፋን ስርዓቶችን እናቀርባለን ብለዋል።
ለሁለት ቀን በቆየው የማስተዋወቂያ ፕሮግራም ላይ ከዱባይ የመጡት የጆቱን ቲክኒካል ስፔሻሊስት አቶ አህመድ ክህታብ ስለ ህንጻ ወለል ግንባታ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በኢትዮጵያ የግንባታና የማጠናቀቂያ ኢንዱስትሪ የበለጠ ብሩህና ፈጠራ ያለው ለማድረግ በጋራ ለመስራት በመድረኩ ጥሪ ቀርቧል።




