banner

የ10 አመት ታዳጊ በነብር ተበልቶ ሞቶ መገኘቱን ፖሊስ ገለፀ ።

#FastMereja I በድሬደዋ ከተማ ዙሪያ አዋሌ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ገንደ ሳሊ ተብሎ በሚጠራው መንደር ህዳር 8 ቀን 2018 ዓ/ም ከንጋቱ 12 ሰአት ገደማ የ10 አመት ታዳጊ በነብር ተበልቶ መሞቱ ተነገረ።

የቢየ አዋሌ ፖሊስ ጣቢያ አዛዥ ኢ/ር አብዱሰላም መሀመድ ለድሬ ፖሊስ ሚዲያ እንደገለፁት ሞች ገመዳ አብደላ የተባለው የ10 አመት ታዳጊ ህዳር 7 ቀን ከምሽቱ 12 ሰአት ገደማ ከቤት እንደወጣ ባለመመለሱ ቤተሰቦቹ ምሽቱን ሲያፈላልጉት ቢቆዩም በንጋታው ጠዋት 12 ሰአት ላይ በነብር እየተበላ ቢያገኙትም ህይቱን ማትረፍ አለመቻላቸውን አና ታዳጊው ሞቶ ማግኘታቸውን ገልፀዋል ።

ፖሊስ በበኩሉ በአካባቢው ነብር መኖሩን እና ከአሁን በፊትም በተደጋጋሚ ግዜ ጥቃት ማደረሱን አስታውሶ የአከባቢው ማህበረሰብ በተለይ ልጆችን ብቻቸውን ከመልቀቅ በመቆጠብ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ መልዕክቱን አስተላልፏል ።

Leave a Comment