banner

የኢትዮ ጃዝ ኢንስትሩመንታል አልበም ሊለቀቅ ነዉ!

#FastMereja I በሙዚቀኛ መሐመድ ራጁ የተሰራዉ “ብርሃን” የተሰኘ ኢንስትሩመንታል የሙዚቃ አልበም ህዳር 19/2018 ዓ.ም እንደሚመረቅ በዛሬዉ እለት በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

ይህን ለየት ያለ ኢንስትሩመንታል አልበም ሰርቶ ለማጠናቀቅ አንድ ዓመት ፈጅቷል ይህ የሙዚቃ አልበምም 11 የሙዚቃ ስብስቦችን ይዟል።

ከዚህ ቀደም ሰላምታ የተሰኘ የመጀመሪያ አልበሙን በ2010 ዓ.ም ለአድማጭ ማድረሱ ይታወቃል፣ “ብርሀን” የተሰኘው ሁለተኛ አልበሙ በኪቦርድ፣ ቤዝ፣ አኮስቲክ ጊታር፣ ክራር፣ የሙዚቃ መሳሪያዎች የተሰሩ የሙዚቃ ስራዎች እንደያዘ ተገልጿል።

ሙዚቀኛ መሐመድ የሙዚቃ ኪቦርድ መጫወት የጀመረው 1998 ዓ.ም ሲሆን ሶስት ዓመት አፍሪካ ጃዝ ስኩል ( ጃዝ አምባ ) ተምሯል።

ሙዚቀኛ መሀመድ ራጁ ከዚህ ቀደም በተለያዩ ናይት ክለቦች እንደሰራ በጣም ብዙ የአረብ አገሮች ለሙዚቃ ኮንሰርት ከኤፍሬም ፣ ሀመልማል ፣ ንዋይ ፣ ሀይማኖት ግርማ ፣ ፍቅር አዲስ እና ሌሎች ዘፋኞች ጋር የመስራት እድሉ አጋጥሞት እንደነበር በዛሬዉ እለት በተሰጠዉ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ተናግሯል።

ከትግርኛ ዘፋኞች መሀል የአብረሀም ገብረመድህን ፣ የማህሌት ገብረጊዮርጊስ ፣ የሸዊት መዝገቦ ኪቦርዲስት በመሆን የተለያዩ ሀገራት እንደሄደም አያይዞ ገልጿል።

አልበሙ ህዳር 19/2018 ዓ.ም በትሪፕል ሆቴልና ስፓ ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት ይመረቃል።

#ኪነ_ጥበብ ዘገባ




Leave a Comment