#FastMereja I በስልጤ ዞን ወራቤ ከተማ አስተዳደር በከባድ የውንብድና ተግባራት የተከሰሱ ግለሰቦች እስከ 16 ዓመት በሚደርስ ጽኑ እስራት እና በገንዘብ እንዲቀጡ የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ውሳኔ አስተላለፈ።
ተከሳሾቹ በቡድንና በተናጠል ሆነዉ በወራቤ ከተማ ልዩ ልዩ ሰፈሮች በመዟዟር ከታህሳስ 2015 ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 2016 በተለያዩ ጊዜያት ከተለያዩ የግል ተባዳዮች ከዘመናዊ ሞባይል ዝርፊያ እስከ እስከ ንብረት ማውደምና ድብደባ፣ የጸጥታ አካላትን ከመደብደብ የተለያዩ ግለሰቦች ላይ ዛቻና ማስፈራሪያ የዘለቀ ተደጋጋሚ የውንብድና ተግባራት መፈጸማቸውን የሚያትቱ 22 ክሶች መመስረታቸውን በውሳኔ ዝርዝር ላይ ተመላክቷል።
የስልጤ ዞን ፍትህ መምሪያ አቃቤ ህግ ከፖሊስ ተጣርቶ በቀረበለት መረጃ መሰረት የመሰረተውን ክስ ሲመለከት የቆየው የስልጤ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ህዳር 11/2018 በዋለው ችሎት ከ18 ተከሳሾች ውስጥ 3ቱ በነጻ ሲሰናበቱ 8ቱ በ2 አመት የገደብ ቅጣት፣ 7 ተከሳሾች በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።
1ኛ – ተከሳሽ አብድሽኩር ሙባሪክ ኑርሰቦ 16 አመትና 4 ሺህ ብር
2ኛ – ተከሳሽ ኢዘዲን ዋበላ ኢብሮ 7 ዓመት ከ9 ወር እና 1 ሺህ ብር
3ኛ – ተከሳሽ አብዱሰላም ከማል አህመድ 8 አመት ከ4 ወርና 1 ሺህ ብር
4ኛ – ተከሳሽ አብዱልሃፊዝ ሱልጣን መሀመድ 2 ዓመት ከ6 ወር
5ኛ – ተከሳሽ ከማል ራህመቶ 2 ዓመት ከ6 ወር
9ኛ – ተከሳሽ ሙዲን ተውፊቅ ላሉ 3 አመት እና 1 ሺህ ብር በጽኑ እስራት እንዲቀጡ ሲወሰን፣
14ኛ – ተከሳሽ አብዱረዛቅ ሸይቾ ከዚህ ችሎት ቀደም ባሉ ቀናት በተሰየመው ችሎት 4 ዓመት ከ 3 ወር በጽኑ እስራት እንዲቀጣ ከፍተኛ ፍርድ ቤቱ መወሰኑ ከስልጤ ዞን ፖሊስ መረጃ ያመለክታል።
