0
#FastMereja I የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ባለሙያ የሆኑት አቶ ቻላቸው ጌጡ በስህተት ወደ ባንክ ሒሳብ ቁጥራቸው የገባውን 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር በታማኝነት ለባለቤቱ መልሰዋል፡፡
ህዳር 13 ቀን 2018 ዓመተ ምህረት ከአዋሽ ባንክ አቶ አብዱል ሰመድ መሃመድ የተባሉ ደንበኛ ወደ አሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ለአቶ መሃመድ ኢብራሂም 8 ነጥብ 4 ሚሊዬን ብር እንዲላክላቸው ጥያቄ ቢያቀርቡም ገንዘቡ በስህተት ወደ አቶ ቻላቸው ጌጡ አካውንት ገቢ ሆኗል፡፡
አቶ ቻላቸው ጌጡ በስህተት ወደ ሒሳብ ቁጥራቸው የገባውን ገንዘብ በታማኝነት ለባለቤቱ ተመላሽ በማድረግ አርዓያነት ያለው ተግባር ፈጽመዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ላሳዩት ታማኝነት እና አርዓያነት ያለው ተግባር አቶ ቻላቸው ጌጡን አመስግኗል።

3 comments
ምን ይባላል እሺ ይሄ
እናቱ ስትመርቀው አሜን ሳይል የቀረ ሰው😭
የኔ እድል እንደ ቁ*ዬ የተዘቀዘቀ ነው😥 ምን አለ ለኔ ባረገው መመለሱን ፈጣሪ ነበር ሚያቀው