banner

“ሰግጥ ፈምስ” በማለት በየመንገዱ ህብረተሰቡን ሲያስደንግጥ የነበረው ጨምሮ ሌሎች ቲክቶከሮች ታሰሩ

#FastMereja I የማህበራዊ ሚዲያን በኃላፊነት በመጠቀም ትውልድን ማነፅ እንደሚገባ የበርካቶች ሀሳብና አስተያየት ከመሆኑም አልፎ ዜጎች ያልተገራ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀም እንዲገታ በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ሀሳቦቻቸውን እየሰጡም ይገኛሉ፡፡

የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያም የማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ሙያዊ ክብርን የሚያዋርዱ፣ ከህብረተሰቡ ባህል፣ እምነትና ሞራል ተቃራኒ የሆኑ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ የነበሩ ” የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪዎች ነን ” (Social Media Influencers and Content Creators) የሚሉ አራት ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራ ይገኛል፡፡

የመጀመሪያዎቹ ተጠርጣሪዎች ዛሀራ መሀመድና ፈቲያ ኤልያስ የተባሉ ነዋሪነታቸው በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ቦሌ ቡልቡላ ሲሆን የቲክቶክ ፕላትፎርምን በመጠቀም የሀገሪቱን ባህል፣ ወግ፣ እምነትና ሞራል በማይመጥን መልኩ “Illuminant” ወይም ” የሠይጣን ማህበርተኞች አባላት ነን እኛን ምሰሉ፤ በርካታ ገንዘብ ታገኛላችሁ” የሚሉ መልዕክቶችን ሲያስተላልፉ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ሦስተኛው ተጠርጣሪ ደግሞ ለታ ደረጄ ተረፋ የተባለ ነዋሪነቱ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ወረዳ 04 ልዩ ቦታው ጀሞ ሦስት የሆነ ” የተከበረውን የመምህርነት ሙያና የመምህራንን ክብር በሚያንቋሽሽ መልኩ” ተንቀሳቃሽ ምስሎችን እየሰራ በቲክቶክ ፕላትፎርም ሲያሰራጭ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፤ ተጠርጣሪው በሚለቃቸው ተንቀሳቃሽ ምስሎች የተማሪ የደንብ ልብስ ለብሶ የመማሪያ ወንበሮች ላይ ቆሞ መጨፈር፣ በመምህራን ላይ የማሾፍ፣ ከተማሪ ኪስ ገንዘብ የመስረቅና የመሳሰሉ ይዘቶችንም ይሰራ እንደነበር ፖሊስ አረጋግጧል፡፡

አራተኛው ተጠርጣሪ ኤዶም ሚሊዮን ሲሆን ነዋሪነቱ በቂርቆስ ክ/ከተማ ወረዳ 10 ልዩ ቦታው ካምቦሎጆ እንዲሁም የሽመልስ ሀብቴ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ሲሆን እርሱም የቲክቶክ ፕላትፎርምን በመጠቀም ከወገቡ በላይ ልብሱን በማውለቅና ራቁቱን በመሆን “ሰግጥ ፈምስ” በማለት በየመንገዱ ህብረተሰቡን የማስደንገጥ፣ ራቁቱን ምግብ በትሪ በመያዝ ህብረተሰቡን ካላጎረስኳችሁ የማለትና የማስደንገጥ ይዘቶችን ሲሰራ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ፖሊስ በቁጥጥር ስር በዋሉ ግለሰቦች ወይም “የማህበራዊ ሚዲያ አንቂ ወይም ይዘት ፈጣሪዎች ነን” (Social Media Influencers and Content Creators) በሚሉ ግለሰቦች ላይ ተገቢውን የወንጀል ምርመራ ስራ የጀመረ ሲሆን በቀጣይም ተመሳሳይ ድርጊት ውስጥ የሚገቡ የማህበራዊ ሚዲያ “አንቂ ነን” ባዮችን እንደማይታገስም የአዲስ አበባ ፖሊስ ጠቅላይ መምሪያ ያሳስባል፡፡





10 comments

Shemsiya Endris December 17, 2025 - 5:34 pm

ችግሩ ሳምንት ታስረው Dear Mama ብለው ተነቅሰው ይወጣሉ።

Reply
Biruk Fekede December 17, 2025 - 5:35 pm

አብሻሎ 😂

Reply
Teddy Demeke December 17, 2025 - 5:36 pm

መንግስት በጥቃቅን አጀንዳ ሞታችንን ርሀባችንን ኑሮ ውድነትን የሚያስረሳን ገብቶን ግራ የገባን ህዝቦች ነን ።

Reply
Robi Man Tirusew December 17, 2025 - 5:36 pm

እድሜ ልካቸውን ትውልድን ለማስታማር ደፋ ቀና ሲሉ የነበሩት መምህራኖቻችን ላይ የሚቀልዱት ለሕግ ማቅረባቸው ትክክለኛ እርምጃ ነው ግን ምን ያደርጋል ነገ ጧት ይለቀቃሉ ።

Reply
Bedilu Z Ewunet Ethiopia December 17, 2025 - 5:36 pm

አብሻሎ😂😂😂

Reply
Nuredin Fujaga Bridge December 17, 2025 - 5:37 pm

ስፖንጅ ይዞ ድንጋይ በማስመሰል የሚወረውር እና ብዙዎቹን የሚያስደነግጥ አለ ሰላም ቢባል

Reply
Vet Journey December 17, 2025 - 5:38 pm

ቲክቶክ እራሱ ካልታሰረ እብደቱ የሚቆም አይመስልም!

Reply
Melese Dejenie December 17, 2025 - 5:38 pm

አማራ ናቸው ማለት ነው

Reply
Beharu Beregna December 17, 2025 - 5:38 pm

አሁንም እኮ ፈመሱዋሉ አልተወቀባቹም እንጅ

Reply
Melese Babiso December 17, 2025 - 5:38 pm

በአስቸኳይ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው

Reply

Leave a Comment