0
#FastMereja I ሪች ፎር ቼንጅ (Reach for Change) በ”ግሪን ኢኖቬሽን” ዘርፍ የተሰማሩ ወጣት ስራ ፈጣሪዎች የንግድ ሃሳባቸውን ለባለሙያ ዳኞችና ለባለሃብቶች ያቀረቡበት መድረክ ዛሬ አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ ወጣቶች በከተማችን የሚወጡ ቆሻሻዎችን (በተለይም ፕላስቲኮችን) ወደ ጠቃሚ ምርቶች በመቀየር፡
✅ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የሚያግዙ፣
✅ አዳዲስ የስራ እድሎችን የሚፈጥሩ፣
✅ እንዲሁም ራሳቸውን መቻል የሚያስችሉ የንግድ ሃሳቦችን ይዘው ቀርበዋል።
”አላማችን ወጣቶች ያላቸውን ፍላጎት ወደ መሬት ወርዶ የሚሰራ ቢዝነስ እንዲቀየር መርዳት ነው” ያሉት የሪች ፎር ቼንጅ ካንትሪ ማኔጀር መቅድም ጉልላት፣ ድርጅታቸው እስካሁን 75 ስራ ፈጣሪዎችን በማብቃት ግቡን ማሳካቱን ገልጸዋል።
የሪች ፎር ቼንጅ ድጋፍ ምን ምን ያካትታል?
🔹 የቢዝነስ አመራር እና የፋይናንስ ስልጠና
🔹 የህግ ማዕቀፎች ግንዛቤ
🔹 የገበያ ትስስር እና የኢንቨስትመንት ድጋፍ ማመቻቸት
እነዚህ ወጣቶች ከስልጠናው በኋላ የራሳቸውን ቢዝነስ በይፋ በመጀመር ለአካባቢያቸውና ለሀገራቸው ተፅዕኖ ፈጣሪ ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል።




