banner

በሚሊዮኖች የሚጠበቀው መንፈሳዊ ኹነት

​#FastMereja : ዛሬ በመዲናዋ እምብርት በሚገኘው ታሪካዊው የመስቀል አደባባይ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ምዕመናን በጉጉት ሲጠብቁት የነበረው “የአእላፋት ዝማሬ” በታላቅ ድምቀት ይካሄዳል። ይህ መርሐ-ግብር ከዝማሬው ባለፈ የቤተክርስቲያኒቱን አንድነትና መንፈሳዊ ጥንካሬ ለዓለም የሚያሳይ አጋጣሚ እንደሚሆን ይጠበቃል።

​በሺዎች የሚቆጠሩ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን በአንድ ዓይነት ልብስና ድምፅ በመታጀብ፣ ጥንታዊና ዘመናዊ ያሬዳዊ መዝሙራትን ያቀርባሉ።

​ከሁሉም የአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት የተሰባሰቡ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ምዕመናን አደባባዩን በነጭ ልብስ እንደሚያስውቡት ይጠበቃል።

ዝግጅቱ በተለያዩ በበርካታ የቴሌቪዥን ጣቢያዎችና በማኅበራዊ ሚዲያዎች ለዓለም አቀፍ ምዕመናን በቀጥታ ይተላለፋል።

4 comments

Wiz Acativist January 6, 2026 - 5:33 am

ወንዶች መምጣት አይችሉም?

Reply
Geremew Gedefaw Alemu January 6, 2026 - 5:34 am

ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ሀይማኖት ለዘላለም ትኑር ፈተና ቢበዛባትም ማንም ቢሰድባትም ማንም ቢያሳድዳትም እንደገና ታብባለች እንደ እኔ የመንፈስ ቅናት ያለበት ማነዉ?

Reply
Teach Habitu January 6, 2026 - 5:35 am

እኔ አሁን ልሂድ ልቅር እያልኩ ገና እያሰብኩ ነው

Reply
Natanem Ataro January 6, 2026 - 5:35 am

እንዴት እንደምወደው

Reply

Leave a Comment