#FastMereja l አባይ ቀለም ሰለ ምርቱ ሙያዊ የስልጠና እንዲሁም ፣ የምርት ማመልከቻዎችን የማብራራት እና ከአባይ ቀለም ጋር በቅርበት ለዓመታት የሰሩ ባለድርሻ አካላትን እውቅና ምስጋና መርሀ-ግብር በዛሬዉ እለት አካሂዷል።
አባይ ቀለም በዛሬዉ እለት ለባለድርሻ አካላት፣ ለቀለም ቀቢዎች እና ለአጠቃላይ የቀለም ባለሙያዎች ነዉ ‘የምርት ማሰልጠኛ እና የምክክር መድረክ ነዉ የተካሄደዉ።
የዚህ ዝግጅት ዓላማ ሙያዊ ስልጠና መስጠት፣ የምርት ማመልከቻዎችን ማብራራት እና ከአባይ ቀለም ጋር በቅርበት ለዓመታት የሰሩ ባለድርሻ አካላትን እውቅና ምስጋና መስጠት መርሀ-ግብር መሆኑ ተገልጿል፡፡
የአባይ ቀለም በዲኮሬቲቭ (Decorative)፣ በወተርፕሩፍ (Waterproofing)፣ በእንጨት (Wood)፣ በአውቶሞቲቭ (Auto) እና በኢንዱስትሪ ምርቶች (Industrial category) የሚታወቅ እና
በመንግስት ዋና ዋና ትላልቅ ግንባታዋች እንዲሁም የግል ሜጋ ፕሮጀክቶች ከፍተኛ ጥራት ያለው ምርቶችን በማቅረብ ረገድ ባለው ጠንካራ ስኬት እንደሚታወቅ ተገልጿል።
በዝግጅቱ ላይ አባይ ቀለም ስለ ምርት ቴክኖሎጂ፣ የአተገባበር ዘዴዎች፣ የምርቱን ቁልፍ ባህሪያት እና ጥቅሞች እውቀትን በማካፈል ለጥራት፣ ፈጠራ እና አጋርነት ያለውን ቁርጠኝነት በዚህ መድረክ ገልጿል።




