banner

የደራሲ እና ጋዜጠኛ መርዕድ እስጢፋኖስ ሁለት የልቦለድ መፅሀፍት ለአንባብያን በቁ!

#FastMereja I በጋዜጠኛና ደራሲ መርዕድ እስጢፋኖስ የተጻፉት ሎዛ ዘፀአት(2014 ዓ.ም) እና የሎዛ ድርሳናት(2017 ዓ.ም) ተከታታይ ረጅም ልቦለድ መጻሕፍት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መጻሕፍ ኤጄንሲ(ወመዘክር) ተመርቋል።

የመጻሕፍቱ ይዘት በኢትዮጵያ ሚሊኒዬም ዋዜማ ከአፍሪካ እስከ አውሮፓ የሚዘልቅ ሲሆን በገጸ ባህሪያቱ ሙግት በፍቅር፣ በባህልን እና ስነ ልቦናዊ ጉዳዮች ላይ ይፈላሰፋል ፣የስደት ገጠመኞችን ያስቃኛል እንዲሁም በቀልብ አንጠልጣይ ትረካ የገጸ ባህሪያቱን መጨረሻ ለማወቅ የሚያጓጓ መፅሀፍ መሆኑ ተገልጿል።

የሎዛ ዘፀአት መፅሐፍ የገፅ ብዛት 557 እና የሎዛ ድርሳናት በ517 ገፆች የተቀነበቡ ናቸዉ።

በመፅሀፍ ምርቃቱ የመጽሐፍ ዳሰሳ በጋዜጠኛና ደራሲ ታምሩ ከፈለኝ ቀርቧል።

በዚህ መፅሀፍ ምርቃት ላይ ጸሐፊ ተውኔት አያልነህ ሙላቱ፣ ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ ደራሲት የዝና ወርቁ እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች በመፅሀፉ ዙሪያ ያላቸዉን አስተያየት ሰተዋል።

ሎዛ ዘፀአት(2014 ዓ.ም) እና የሎዛ ድርሳናት(2017 ዓ.ም.) መፅሐፍቶች ሲመረቁ ልዩ ተጋባዥ እንግዶች ፣ ታዋቂ የኪነ-ጥበብ ሰዎች ፣ የጋዜጠኛና ደራሲ መርዕድ እስጢፋኖስ ቤተሰቦች አብሮ አደጎች አድናቂዎች ፣ወዳጆች ጥሪ የተደረገላቸው ታዳሚያን ተገኝተዋል፡፡





Leave a Comment