0
#FastMereja I የፈንድቃ ባህል ማዕከል መስራችና የውዝዋዜ ጠቢቡ መላኩ በላይ፣ በሥነ-ጥበብ ዘርፍ ላበረከተው ዓለም አቀፍ አስተዋጽኦ የፈረንሳይ መንግሥትን ከፍተኛ የክብር ሜዳሊያ ተቀዳጀ።
አርቲስቱ “ኦፊሴር ዴ ላ ኦርደሬ ዴስ አርትስ እና ዴስ ሌትረስ” (Officier de l’Ordre des Arts et des Lettres) የተሰኘውን ሜዳሊያ የተቀበለው፣ በአዲስ አበባ በሚገኘው የፈረንሳይ ኤምባሲ በተካሄደ ሥነ-ሥርዓት ላይ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሚ ማሬሾ እጅ ነው።
ይህ ሽልማት እ.ኤ.አ. ከ1957 ጀምሮ በፈረንሳይ የባህል ሚኒስቴር የሚሰጥ ሲሆን፣ በመላው ዓለም በሥነ-ጥበብ የላቀ ተፅዕኖ ላሳረፉ ግለሰቦች የሚበረከት ከፍተኛ ዕውቅና ነው። አርቲስት መላኩ ሽልማቱን ባገኘበት ወቅት ባስተላለፈው መልዕክት፤ “ይህ ክብር እኔንና ፈንድቃን ለደገፉን ሁሉ ነው፤ ስኬቱም የጋራ ነው” ሲል ገልጿል።
መላኩ በላይ የኢትዮጵያን ባህላዊ ውዝዋዜና ሙዚቃ በዓለም መድረክ በማስተዋወቅ ረገድ ግንባር ቀደም ተጠቃሽ አርቲስት ነው።
