banner

የጌዴኦ ዘመን መለወጫ “ዳራሮ” በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

#FastMereja I የጌዴኦ ብሔር የዘመን መለወጫ “ዳራሮ” በዓል “ዳራሮ ለባህልና ለቱሪዝም ዕድገት” በሚል መሪ ቃል በአዲስ አበባ በሸራተን አዲስ ሆቴል በድምቀት ተከብሯል። በበዓሉ አከባበር ላይ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ አርቲስቶችና ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል።

በዓሉ የጌዴኦን ብሔር ማንነትና ጥንታዊ የሀገር በቀል እውቀትን ለዓለም የሚያስተዋውቅ ከመሆኑም ባለፈ፣ ለሀገሪቱ የቱሪዝም ሀብት ትልቅ ግብዓት እየሆነ ይገኛል። በአሁኑ ወቅትም ይህንን ድንቅ የባህል እሴት ሳይበረዝ ለትውልድ እንዲተላለፍና በዓለም የትምህርት፣ የሳይንስና የባሕል ድርጅት (ዩኔስኮ) እንዲመዘገብ ሰፊ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

ዳራሮ ከአካባቢ አልፎ በሀገር አቀፍ ደረጃ መከበሩ የጌዴኦን ዞን ከማስተዋወቅ ባለፈ፣ በዞኑ ያለውን የኢንቨስትመንት አማራጭ ለማሳደግ ከፍተኛ ሚና እንደሚጫወት ታምኖበታል። በበዓሉ ላይ የተገኙ የመዲናዋ ነዋሪ የብሔሩ ተወላጆችም፣ በዓሉ በአዲስ አበባ መከበሩ ባህላቸውን ለማጉላትና አንድነታቸውን ለማጠናከር ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።





Leave a Comment