0
#FastMereja I የትግራይ ክልል አክቲቪስት የሆነው አሉላ ሰለሞን፣ በአሁኑ ወቅት በትግራይ ክልል የታየውን የጦርነት እንቅስቃሴ በመቃወም “ጦርነትን እንጠየፍ” (Say No to War) የሚል መልዕክት በማኅበራዊ ገጹ ላይ አጋራ።
አክቲቪስቱ በይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባሰፈረው መልዕክት፣ ዳግም ወደ ጦርነት መግባት እንደማይገባና የጦርነትን አውዳሚነት በመጥቀስ ተቃውሞውን ገልጿል።
አክቲቪስቱ ከሁለት ዓመት በፊት በነበረው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት “ጦርነት ባህላዊ ጨዋታችን ነው” በማለት በሰጠው አስተያየት በወቅቱ ከፍተኛ ትችትና ተቃውሞ ሲስተናገድበት እንደነበር ይታወሳል።
