#Fastmereja: ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል አዘጋጅነት የአካባቢ ጥበቃ ጉዳይን በተመለከተ “Uniting for a Greener Planet” – “ለአረንጓዴ ምድር በአንድነት መተባበር” በሚል መሪ ቃል የውይይት እና የልምድ ልውውጥ መድረክ በዛሬዉ እለት ተካሄደ።
በመድረኩ ከ25 በላይ የሆኑ ት/ቤቶች የአካባቢ ጥበቃ በት/ቤቶች ተግባራዊ የሚሆንበትን ጉዳይ አስመልክቶ በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸዉን ስምምነትም ፈፅመዋል።
ትምህርት ቤቱ ባዘጋጀው በዚህ ጉባኤ ላይ ከ25 በላይ ት/ቤቶች ተወካይ ያሳተፉ ሲሆን የተለያዩ ትምህርት ቤቶች ሀላፊዎች፣ የት/ቤቱ ከፍተኛ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
በአየር ንብረት ለውጥና በአካባቢ ጥበቃ ላይ ከስር ጀምሮ ልጆችን እውቀት ማስታጠቅ ለተፈጥሮ ፍትሃዊነት እንዲቆሙና አካባቢያቸውን መጠበቅ ላይ ትኩረት እንዲያደርጉ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የትምህርት ቤቱ መስራችና ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ዘላለም አማረ ተናግረዋል፡፡
ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል ማህበራዊ ግዴታውን እየተወጣ እንደሚገኝና በተማሪዎቹ በኩል 5 በመቶ ለሚደርሱ አባውራዎች ንፁህ የመጠጥ ውሀ እንዲያገኙ ማድረጉን አቶ ዘላለም አክለዉ ገልፀዋል።
ከተለያዩ ትምህርት ቤቶችና ከ “Nature Lovers of Ethiopia ኢኒሼቲብ የመጡ ተማሪዎች ባቀረቡት ሐሳብ ተፈጥሮ በዋናነት የምትጎዳባቸው መንገዶች የፕላስቲክ ምርት መስፋፋት፣የደን ጭፍጨፋና የጋዝ ልቀት (immission) እንደሆኑ ገልፀው ልጆች በነዚህ ምክንያቶች የሚደርሰውን የተፈጥሮ ጉዳት በመከላከልና ድምፅ በመሆን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ በማበርከት ምቹ ከባቢን መፍጠር እንደሚገባ ተገልጿል።
ዋን ፕላኔት ኢንተርናሽናል ስኩል ከተመሠረተ 2ዐኛ ዓመቱን ያስቆጠረ ሲሆን ከ4ዐዐ በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች ነፃ የትምህርት እድል እንደሰጠ እና ከ1 ሺህ 200 በላይ ተማሪዎችን እያስተማረ እንደሚገኝ ገልፀዋል።




