banner

የማልበርግ ቫይረስ በሸታ ወረርሽኝን ከመቆጣጠር ጋር ተያይዞ የእውቅና ፕሮግራም ተካሄደ

#Fastmereja I የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የማርበርግ በሽታን ለማጥፋት በተደረገው ርብርብ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ለጤና ባለሙያዎች፣ አመራሮች እንዲሁም ባለ ድርሻ አካላት የእውቅና እና ሽልማት መርሀ-ግብር በስካይ ላይት ሆቴል አካሂዷል።

የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከጤና ሚኒስቴር እና ከአጋር አካላት ጋር በመተባበር፣ በሀገራችን ተከስቶ የነበረውን የማርበርግ ቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ በሁሉም ባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ትብብር፣ በጠንካራ የአመራርና የማስተባበር ጥበብ እና በጤና ባለሙያዎች ፊታውራሪነት ወረርሽኙን በአጭር ጊዜ በተሳካ ሁኔታ መቆጣጠር መቻሉ ተገልጿል።

የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ በፕሮግራሙ የመክፈቻ ንግግራቸው ወቅት እንደገለፁት ኢትዮጵያ በሽታውን የተቆጣጠረችበት ውጤታማ ተግባር ዜጎች ከተባበሩ ማሳካት የሚሳናቸው ነገር እንደሌለ ሁነኛ ማሳያ መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢኒስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር መሳይ ሀይሉ በበኩላቸው፤የማርበርግ ቫይረስ በሽታን ለመቆጣጠር በተከናወኑ ተግባራት ለጤና ሥርዓቱ አቅም የሚሆኑ ትምህርቶች መገኘታቸዉን ገልፀዋል።

በእዉቅና አሰጣጥ ፕሮግራሙ ላይ በተገኙ ተሞክሮዎች እና የወደፊት አቅጣጫ ዙሪያ የፓናል ዉይይት ተደርጓል።

በመርሀ-ግብሩ ላይ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የጤና ባለሙያዎች፣ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች ተገኝተዋል።





Leave a Comment