#FastMereja I በማንችስተር ዩናይትድ ስታዲየም (ኦልድ ትራፎርድ) ጥላ ስር የሚገኘው እና በደጋፊዎች ዘንድ በስፋት የሚታወቀው “ዘ ዩናይትድ ካፌ” (The United Café)፣ በውስጡ በተገኘ ከፍተኛ የአይጥ ወረርሽኝ ምክንያት የ10,000 ፓውንድ ቅጣት እንደተጣለበት ዴይሊሜል ዘግበዋል።
የጤና ተቆጣጣሪዎች ባደረጉት ድንገተኛ ፍተሻ፣ አይጦች የገመጧቸው ድንቾች እና በምግብ ማብሰያ ክፍሎች ውስጥ የአይጥ ቆሻሻዎች ተገኝተዋል።
በዚህም ምክንያት ካፌው ዝቅተኛው የሆነው የ”ዜሮ ኮከብ” የንፅህና ደረጃ ተሰጥቶታል። አንድ የጤና ተቆጣጣሪ ማንነቱን ደብቆ “የግሉተን አለርጂ አለብኝ” ብሎ ምግብ ባዘዘበት ወቅት፣ ካፌው አለርጂውን ግምት ውስጥ ሳያስገባ ግሉተን ያለበት በርገር በማቅረቡ ሌላ ጥሰት ተመዝግቦበታል።
ካፌው እና አጠገቡ የሚገኘው “ሌጀንድስ” የተሰኘው መጠጥ ቤት ለጊዜው ተዘግተው ጥልቅ የፅዳት ስራ እና የአይጥ መከላከያ ስራዎች እንዲሰሩ ታዘዋል።
ይህ ካፌ ከማንችስተር ዩናይትድ ክለብ ጋር በቀጥታ ግንኙነት የሌለው ቢሆንም፣ በጨዋታ ቀናት በደጋፊዎች እጅግ የሚዘወተር ቦታ ነው። የትራፎርድ ካውንስል ባወጣው ሪፖርት መሰረት፣ ፍተሻው የተካሄደው እ.ኤ.አ በነሀሴ 2024 በአካባቢው የአይጥ እንቅስቃሴ መታየቱን ተከትሎ ነበር።
