banner

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በአርሲ የደረሰውን ጥቃት አወገዘ

​#FastMereja I የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን ሺርካ ወረዳ በንፁሐን የኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች ላይ የደረሰውን አሰቃቂ ጥቃት በፅኑ ማውገዙን ገለጸ።

​ምክር ቤቱ ባወጣው መግለጫ፣ በደረሰው አሰቃቂ አደጋ ማዘኑን ገልጾ፣ ድርጊቱ ማንኛውንም ሃይማኖት የማይወክልና እኩይ ዓላማ ያለው መሆኑን አመልክቷል። ድርጊቱ በሃይማኖቶች መካከል ለዘመናት የቆየውን የመከባበር እሴት በመናድ፣ በአማኞች መካከል ጥርጣሬና ግጭት ለመፍጠር የታለመ “እኩይ ሴራ” ነው ብሎ እንደሚያምን ገልጿል።

መንግስት ድርጊቱን የፈጸሙ አጥፊዎችን በአፋጣኝ ለይቶ ተገቢውን ህጋዊ እርምጃ እንዲወስድ ጥሪ አቅርቧል። በሃይማኖቶች መካከል ያለውን ሰላምና መከባበር ለማፍረስ የሚሰሩ አካላትን ህዝቡ በንቃት ሊከላከል እንደሚገባ ተመልክቷል።

​ምክር ቤቱ ለሟች ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች “አላህ መፅናናቱን ይስጣቸው” በማለት ፀሎቱንና መልካም ምኞቱን አስተላልፏል።

Leave a Comment