0
#FastMereja I የኢራን ወታደራዊ ጥቃት በኩዌት ላይ ከተሰነዘረበት ጊዜ ጀምሮ 178 የባሊስቲክ ሚሳይሎች እና 384 ድሮኖች ተለይተው መከሸፋቸውን የሃገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር ማክሰኞ ማለዳ ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።
የመከላከያ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ኮሎኔል ሳዑድ አል-አትዋን እንደገለጹት፣ ጥቃቱ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ 27 የኩዌት ጦር አባላት ላይ ጉዳት ደርሷል። የቆሰሉት ወታደሮች ሁኔታ ቀላል ቢሆንም ሁለቱ አሁንም የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው መሆኑን ቃል አቀባዩ አክለው ገልጸዋል።
የኩዌት ጦር ኃይሎች በከፍተኛ ንቃት ላይ እንደሚገኙና በየሰዓቱ የሚከሰቱ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎችን በቅርበትና በጥንቃቄ እየተከታተሉ መሆኑ ተገልጿል።
