banner

ግብፅ በአረብ ሀገራት ሉዓላዊነት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን እንደምትቃወም በድጋሚ ገለጸች

#FastMereja I ​የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በድር አብደላቲ፣ ግብፅ ለአረብ ሀገራት ያላትን ድጋፍ በማረጋገጥ በግዛቶቻቸው ላይ የሚፈጸሙ ማናቸውንም ጥቃቶች እና የሉዓላዊነት ጥሰቶችን እንደምትቃወም አስታወቁ።

ሚኒስትሩ ይህንን የገለጹት ከሳዑዲ አረቢያ፣ ከተባበሩት አረብ ኤምሬትስ፣ ከኦማን እና ከሶሪያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ነው። ይህም አሜሪካ እና እስራኤል ከኢራን ጋር የጀመሩት ጦርነት አምስተኛ ቀኑን በያዘበት ወቅት ነው።
​
እስራኤል እና አሜሪካ በኢራን ወታደራዊ እና የኒውክሌር ተቋማት ላይ መጠነ ሰፊ ጥቃት መፈጸማቸውን ተከትሎ፣ ኢራን በበኩሏ ወደ እስራኤል እና በመካከለኛው ምስራቅ ወደሚገኙ የአሜሪካ ይዞታዎች (ሳዑዲ፣ ባህሬን፣ ኳታር፣ ኩዌት፣ ዮርዳኖስ እና ኤምሬትስን ጨምሮ) የሚሳኤልና የድሮን ጥቃቶችን እየሰነዘረች ትገኛለች።

ሚኒስትር አብደላቲ የአረብ ሀገራት ብሔራዊ ደህንነት የማይከፋፈል መሆኑን የገለጹ ሲሆን፣ ቀውሱ ወደ ቀጠናዊ ጦርነት እንዳይሸጋገር ስጋታቸውን ገልጸዋል።

Leave a Comment