#FastMereja I በሪል ስቴት ዘርፍ ለአሥር ዓመታት በታማኝነት የዘለቀው ቴምርፕሮፐርቲ፣ ከአፍሪካ ኩራት ከሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በመተባበር ለደንበኞቹ ልዩ የጉዞ ዕድል የሚያስገኝ ስምምነት በዛሬዉ እለት ነዉ የተደረገዉ።
ይህ “በቤትዎ ዓለምን ይዙሩ” የተሰኘው አጋርነት፣ የቴምር ደንበኞች ቤት ወይም ሱቅ ሲገዙ በከፈሉት ክፍያ ልክ የሼባ ማይልስ (ShebaMiles) ሽልማት የሚያገኙበት መሆኑ ተገልጿል።
ስምምነቱ የቴምር ሪል ስቴት ደንበኞች በከፈሉት የቤት ወይም የሱቅ ክፍያ ልክ በአየር መንገዱ የጉዞ ማይልስ የሚያገኙበትና የክብር ደረጃቸው የሚያድግበትን ዕድል የሚፈጥር መሆኑተገልጿል።
በዚሁ መነሻ ለቤቱ ዋጋ ከ5ዐ በመቶ በታች ክፍያ የፈጸሙ ደንበኞች ለእያንዳንዱ አንድ ዶላር 2.5 ማይልስ፤5ዐ በመቶና ከዚያ በላይ ክፍያ የፈጸሙ ደግሞ ለእያንዳንዱ አንድ ዶላር 3.5 ማይልስ ተጠቃሚ ይሆናሉ፡፡
ይህ ስምምነት ደንበኞች ለቤት ግዢ የሚያወጡት ወጪ ለቀጣይ ዓለም አቀፍ በረራዎቻቸው እንደ ተጨማሪ ጉርሻ ሆኖ እንዲያገለግላቸው ታስቦ የተዘጋጀ ነው፡፡
በቤት ግዢዎ በሚያገኙት ማይልስ የሼባ ማይልስ ደረጃዎን ከብሉ ወደ ሲልቨር፣ ወይም ወደ ጎልድ በማሳደግ የልዩ መስተንግዶ ተጠቃሚ መሆን ይችላሉ፡፡
በተለይም ይህ ስምምነት በውጭ ሀገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ሀገር ቤት የሚያደርጉትን ጉዞ እጅግ የሚያቀልና ትርፋማ የሚያደርግ አሰራር እንደሆነም ነዉ የተገለፀዉ።
ቴምር ፕሮፐርቲ ዶሃ፣ ዱባይ፣ ሮም፣ በርሊን፣ ፓሪስ እና ዋሽንግተን ዲሲ ከተሞች በመዘዋወር ከደንበኞች ጋርየመቀራረብ ስራን የሰራ ሲሆን በቀጣይም በተለያዩ የኢትዮጵያ ክልል ከተሞች፣ በአውሮፓና አሜሪካ መሰል እንቅስቃሴን ለማድረግ በዝግጅት ላይ ይገኛል፡፡




