0
#FastMereja I የሳውዲ ዓረቢያ መከላከያ ሚኒስቴር ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ ወደ ሀገሪቱ የአየር ክልል የተተኮሱ ዘጠኝ ሰው አልባ አውሮፕላኖችን (ድሮኖችን) መትቶ ማውደሙን በይፋ አስታወቀ። ጥቃቱ ኢላማ ያደረገው የትኛውን አካባቢ እንደሆነና የደረሰ ጉዳት ስለመኖሩ ሚኒስቴሩ እስካሁን በዝርዝር የገለጸው ነገር የለም።
እንደ ሳውዲ መከላከያ ሚኒስቴር መግለጫ ከሆነ፣ የሀገሪቱ የአየር መከላከያ ሰራዊት ወደ ግዛቷ የሚገቡ የጥቃት ድሮኖችን በንቃት በመከታተል ላይ ይገኛል። ባለፉት ጥቂት ሰዓታት ውስጥ የታዩት እነዚህ ዘጠኝ ድሮኖች ወደ አየር ክልሉ ሰርገው ከመግባታቸው በፊት መክሸፋቸው ተገልጿል።
ሚኒስቴሩ ድሮኖቹ የተተኮሱበትን ትክክለኛ አቅጣጫም ሆነ የትኛው አካል ጥቃቱን እንደፈጸመ በይፋዊ መግለጫው ላይ ባይጠቅስም፣ በክልሉ ካለው ወቅታዊ የጸጥታ ሁኔታ አንጻር የየመን አማጺያን (ሁቲዎች) ተመሳሳይ ጥቃቶችን ሲፈጽሙ መቆየታቸው ይታወሳል።
