banner

ኢራን ሊባኖስን አሳልፋ እንደማትሰጥ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን አስጠነቀቁ

​#FastMereja I የኢራኑ ፕሬዝዳንት መስዑድ ፔዜሽኪያን ሀገራቸው ሊባኖስን ብቻዋን እንደማትተዋት በመግለጽ፣ እስራኤል በሊባኖስ ላይ የምትፈጽመው ጥቃት የተኩስ አቁም ስምምነቱን “በግልጽ መጣስ” ነው ሲሉ ኮነኑ።

​ፕሬዝዳንቱ እስራኤል ጥቃቷን የምትቀጥል ከሆነ ዲፕሎማሲያዊ ንግግሮች ትርጉም አልባ እንደሚሆኑ አስጠንቅቀዋል። “እጃችን በቃታ ላይ ነው፤ ኢራንም የሊባኖስን ህዝብ አሳልፋ አትሰጥም” ሲሉ ፔዜሽኪያን ያላቸውን ጽኑ አቋም ገልጸዋል።

​ይህ የኢራን ማስጠንቀቂያ የተሰማው ውጥረቱን ለማርገብ ጥረቶች እየተደረጉ ባሉበት ወቅት ሲሆን፣ ድርጊቱ ቀጠናውን ወደ በለጠ ግጭት ሊከተው እንደሚችል ተሰግቷል። እስካሁን ከእስራኤል ወገን ለተሰነዘረው ወቀሳ የተሰጠ ምላሽ የለም።

Leave a Comment