0
#FastMereja I ታዋቂው ድምፃዊ ወንድሙ ጅራ “የኔ ትዝታ” በተሰኘው የሙዚቃ ስራው የትምህርት ቤቱን ታሪክ በማስተዋወቅና ላበረከተው የላቀ አስተዋፅኦ በመድኃኒዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የክብር አምባሳደርነት ሹመት ተሰጠው።
በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኘው የመድኃኒዓለም አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፤ ድምፃዊ ወንድሙ ጅራ ለትምህርት ቤቱ ላበረከተው አዎንታዊ ተጽዕኖ የእውቅና እና የክብር አምባሳደርነት የምስክር ወረቀት አበርክቶለታል።
ድምፃዊው “የኔ ትዝታ” በተሰኘው የሙዚቃ ቪዲዮው ላይ የትምህርት ቤቱን እውነተኛ ታሪክ እና የቀድሞ ትውስታዎችን በማካተቱ፣ ለተቋሙ ታላቅ የፕሮሞሽን ስራ እንደሰራ ተገልጿል።
መጋቢት 27 ቀን 2018 ዓ.ም
