banner

በትግራይ ተምቤን ዓቢይ ዓዲ የኣሸንዳ ባህላዊ በዓል በደመቀ ሁኔታ እየተከበረ ነው

​#FastMereja I በትግራይ ክልል ተምቤን ዓቢይ ዓዲ ከተማ የሚገኙ ልጃገረዶች ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ የኣሸንዳ በዓልን በታላቅ ድምቀት በማከበር ላይ ይገኛሉ።

​የከተማዋ ልጃገረዶች እና ታዳጊዎች በደብረ ሰላም ቅድስት ማርያም ቤተክርስቲያን በመገኘት “ማርያምዋይ ፀሓየ መፂአያ ኮ ዛ መፅብዓየ” በሚሉ ህያው የጸሎትና የምስጋና ዜማዎችና ግጥሞች ታጅበው የበዓሉን ማስጀመሪያ ስነ-ስርዓት አካሂደዋል። ታዳሚዎቹ የነበሩበትን የነሐሴ ጾም ፍጻሜና የፍልሰታ ማርያም በዓልን አስመልክቶ የቀረበው ይህ ምስጋና፣ የዓቢይ ዓዲ ከተማ ነዋሪዎችንና እንግዶችን ቀልብ ስቧል።





Leave a Comment