#FastMereja I በኢትዮጵያ የኪነ-ጥበብ ታሪክ ውስጥ አዲስ ምዕራፍ የከፈተውና በዓይነቱ የመጀመሪያ የሆነው የ”አደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ” የሽልማት ሥነ-ሥርዓት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሙዚየም በታላቅ ድምቀት ተካሂዷል። በጥቅምት 7 ቀን 2019 ዓ.ም በተካሄደው በዚህ ደማቅ መርሃ-ግብር በርካታ የኪነ-ጥበብ ባለሙያዎች፣ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፈጠራ ሰዎችን ጥረት ያከበረና እውቅና የሰጠ ምሽት ሆኖ አልፏል።
ይህ መድረክ ከተለመደው ባህላዊ የጥበብ ዘውግ ባሻገር፣ ይበልጥ ትኩረቱን በዘመናዊና በሙከራ ስነ-ጥበባት ላይ በማድረግ አዲስ የፈጠራ መንገድ ለተከተሉ ባለሙያዎች ትልቅ ዕድል የፈነጠቀ ነው። የመድረኩ መስራች እና አርቲስቲክ ዳይሬክተር ተክሉ አሻግር (ሔኖክ) እንደገለጹት፣ የዝግጅቱ ዋና ዓላማ እስካሁን በቂ ትኩረት ላልተሰጣቸው የኪነ-ጥበብ ዘርፎች የሚገባቸውን እውቅና መስጠትና ነባሩን አሰራር ጥሰው ወደ አዲሱ የፈጠራ ዓለም የገቡ ወጣቶችን ማበረታታት እንደሆነ ገልጸዋል።
በዕለቱ በክብር እንግድነት የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ አቶ ሃፍተይ ገብረእግዚአብሔር እና ምክትል ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሉባባ ጀማል፣ የኪነ-ጥበብ ሥራዎች የህብረተሰቡን እሴት ለማጉላት ያላቸውን ሚና ገልጸው፤ መንግሥት የወጣቱን ትውልድ የፈጠራ አቅም ለማሳደግ አስፈላጊውን የቴክኒክና የፖሊሲ ድጋፍ እንደሚያደርግ አረጋግጠዋል። በምሽቱ ላይ ልዩ ልዩ ባህላዊና ዘመናዊ ውዝዋዜዎች፣ የፋሽንና የሰርከስ ትርኢቶች የቀረቡ ሲሆን፣ ሁነቱ በአዲስ ሚዲያ ኔትወርክ በቀጥታ ስርጭት ለሕዝብ ተላልፏል፤ እንደ ዝግጅቱ አስተባባሪዎች መግለጫ።
የአደይ ኮንቴምፖራሪ አርት አዋርድ ሙሉ የሽልማት ዝርዝር
1. በኮንቴምፖራሪ ሙዚቃ ዘርፍ
ምርጥ የሙዚቃ አቀናባሪ: ዲጄ ደስ
ምርጥ ሴት ዘፋኝ: ሳሌሚያ
ምርጥ ወንድ ዘፋኝ: ሳሞን ዜማስ
ምርጥ ዲጄ: ዲጄ ቲተም
ምርጥ ባለራዕይ ሙዚቀኛ: ሃዲንቆ
2. በኮንቴምፖራሪ ቪዧል አርት (ዕይታ ጥበብ) ዘርፍ
ምርጥ ሰዓሊ: እያዩ ገነት
ምርጥ ቀራፂ: ተፈሪ መኮንን
ምርጥ ባለራዕይ ሽልማት: ያቡ አርትስ
3. በኮንቴምፖራሪ ሰርከስ ዘርፍ
ምርጥ ሰርከስ ዳይሬክተር: ፍፁም መሳይ
ምርጥ ሰርከስ አሰልጣኝ: በሃይሉ ዮሴፍ
ምርጥ ሴት ሰርከስ ትርዒት አቅራቢ: ቤተልሔም ዳዊት
ምርጥ ወንድ ሰርከስ ትርዒት አቅራቢ: ዳግም አይተንህ
የህይወት ዘመን ተሸላሚ: አወቀ እምሩ
4. በኮንቴምፖራሪ ፋሽን ዘርፍ
ምርጥ ሴት ሞዴል: ሰላማዊት ፅሩይ
ምርጥ ወንድ ሞዴል: ዘላለም ተድላ
ምርጥ ዲዛይነር: ፍቅርተ አዲስ
ምርጥ ባለራዕይ ሞዴል: ሩት ይርጋለም
5. በኮንቴምፖራሪ ዳንስ ዘርፍ
ምርጥ ዳንስ ኬሮግራፈር: ሲሳይ ተካልኝ (ሲስኮ)
ምርጥ ሴት ተወዛዋዥ: መቅደስ ደሳለኝ
ምርጥ ወንድ ተወዛዋዥ: ኤልያስ ሽኩር (ኤርሚ ላስታ)
ምርጥ ባለራዕይ ኬሮግራፈር: ልጅ ተመስገን መለሰ
የህይወት ዘመን ተሸላሚ: ታደሰ ወርቁ
6. በኮንቴምፖራሪ አጭር ፊልም ዘርፍ
ምርጥ አጭር ፊልም አሸናፊ: ሲሳይ መለሰ
የህይወት ዘመን ተሸላሚዎች (Lifetime Achievement Awards)
ለሀገራችን የኪነ-ጥበብ ዕድገት ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ዕውቅና የተሰጣቸው ባለሙያዎች፡
ሎሬት ጸጋዬ ገብረመድህን
የዓለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ
መርአሄ ተውኔት ጋሽ አባተ መኩርያ




