#FastMereja I በኮዬ ፈጬ እና በዙሪያው ባሉ አካባቢዎች የሚስተዋለውን የመዝናኛ ቦታዎች እጥረት ይቀርፋል ተብሎ የሚጠበቀው እና በ300 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተገነባው “ከንረቢ ጫላ” ዘመናዊ ሆቴልና ላውንጅ የምርቃት ስነ-ስርዓቱን ማካሄድ ጀምሯል።
የድርጅቱ ባለቤት አባ ገዳ ጫላ ቱፋ እንደገለጹት፤ ከኮዬ አደባባይ ወደ ቱሉ ዲምቱ በሚወስደው መንገድ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (AASTU) ፊት ለፊት የተገነባው ይህ ሆቴል ከጥቅምት 28 እስከ ህዳር 4 ቀን 2019 ዓ.ም ለተከታታይ 7 ቀናት የሚቆይ ህዝባዊ የምርቃት ስነ-ስርዓት ያካሂዳል።
ቀደም ሲል በአርሶ አደርነት፣ በእንስሳት እርባታና በንግድ ስራ ተሰማርተው እንደነበር ያወሱት አቶ ጫላ፤ “የእግዚአብሔር ይበልጣል” የሚል የኦሮምኛ ፍቺ ያለው “ከንረቢ ጫላ” ሆቴል በአሁኑ ወቅት ከ60 በላይ ዘመናዊ የመኝታ ክፍሎችን፣ የVIP እና VVIP አገልግሎቶችን፣ የመመገቢያ አዳራሾችን እና ከ60 በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚያስተናግድ የመሬት ስር ፓርኪንግ ያካተተ ሲሆን በቀጣይ ህንፃውን እስከ 9 ፎቅ የማሳደግ እቅድ ተይዟል።
ሆቴሉ ለአካባቢው ነዋሪዎችና ለደንበኞቹ 100% ኦርጋኒክ የሆኑ የምግብ አይነቶችን ለማቅረብ ከአካባቢው እርሻዎች እና በአዳማ ከሚገኘው የበረት ማደለቢያ ጋር ትስስር መፍጠሩ ተገልጿል። በተጨማሪም ድርጅቱ በዚህ አዲስ ቅርንጫፍ ለ150 ዜጎች የቋሚ ስራ እድል መፍጠሩ ተነግሯል።
በመጨረሻም ሆቴሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲበቃ ከፍተኛ አስተዋጾ ላበረክቱ ግለሰቦች እና ተቋማት አባገዳ ጫላ ምስጋና አቅርበዋል። ሚዲያዎች ለሆቴሉ ምርቃት የሰጡት የሚዲያ ሽፋን አመስግኗል።
📷 ምንተስኖት ሙሉጌታ




