banner

«ሶፊ ፊት ክላሲክ» የሰውነት ቅርፅ ውድድር መጋቢት ወር ሊካሄድ ነው።

#FastMereja I በምስራቅ አፍሪካ ትልቁ የሰውነት ቅርፅ ውድድር የሆነው «ሶፊ ፊት ክላሲክ» (Sofi Fit Classic) በመጋቢት ወር ሊካሄድ መሆኑ ተገለጸ። ሁነቱን በስኬት ለማጠናቀቅም የሶፊ ፊት ክላሲክ ተቋም ከሁለትዮሽ አጋር ከአዲስ አበባ ክብደት ማንሳትና ሰውነት መገንባት ፌዴሬሽን ጋር በጌት ፋም ሆቴል በተከናወነ ሥነ ሥርዓት የጋራ መግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሶፊ ፊት ክላሲክ መሥራችና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሶፎንያስ ነብዩ እንደገለጹት፤ ይህ የፊርማ ሥነ ሥርዓት ለኢትዮጵያ የሰውነት ግንባታና የክብደት ማንሳት ስፖርት አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ታሪካዊ ቀን ነው። የተቋሙ ራዕይ ውድድር ማዘጋጀት ብቻ ሳይሆን ለጀማሪዎችም ሆነ ለልምድ ላላቸው አትሌቶች እኩል የመወዳደር ዕድል የሚፈጥር፣ ፍትሃዊነትንና ሙያዊነትን የሚያስቀድም የተሰጥኦ ማዕከል መገንባት መሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል። አትሌቶች የሚገባቸውን ክብርና ፍትሃዊ የውድድር ዕድል እንዲያገኙ ከመሥራት ባለፈ በተለይም ወጣቶችና ሴቶች በስፖርቱ በስፋት እንዲሳተፉ ሰፊ ጥረት እንደሚደረግ ተመላክቷል።

የስፖርቱን ዘርፈ ብዙ እድገት እውን ለማድረግ የጋራ ትብብርና ኃላፊነት ወሳኝ መሆኑን የገለጹት የስፖርቱ ባለሙያዎችና የፌዴሬሽኑ አመራሮች፤ ከሶፊ ፊት ክላሲክ ጋር የተጀመረው አጋርነት ለአትሌቶች ስኬትና ለወደፊቱ ትውልድ የተሻለ ምዕራፍ እንደሚከፍት ተስፋቸውን ገልጸዋል። በመጋቢት ወር በሚካሄደውና በምስራቅ አፍሪካ ግዙፍ ተሳትፎ ይኖረዋል ተብሎ በሚጠበቀው በዚህ ታላቅ የሰውነት ቅርፅ ውድድር ላይ አሰልጣኞች፣ ዳኞች፣ አትሌቶች እና የስፖርቱ ደጋፊዎች በንቃት እንዲሳተፉ ጥሪ ቀርቧል።





Leave a Comment