0
#FastMereja
ወጣቱ ድምፃዊ የሀበሻን ባህላዊ እሴቶችን እንዲሁም ሐበሻ ቢራን እንዲያስተዋውቅ የተመረጠው በሐበሻ ቢራ ፋብሪካ ነው።
በአንድ አልበም እና በተለያዮ ነጠላ ዜማዎች ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈው ድምፃዊ ዳዊት ፅጌ ብራንድ አምባሳደር ሆኖ በመመረጡ የሀበሻ መገለጫ የሆኑ እሴቶች በዓለም አደባባይ ጎልተው እንዲወጡ ይሰራል።
“እልል ያልኩ ሀበሻ ” በሐበሻ ቢራ አዘጋጅነት የደመቀ ዝግጅት ተካሄዷል።
በቃና ዌርሀውስ በተዘጋጀው በአይነቱ ለየት ያለ ፐሮግራም የኢትዮያዊያን ባሀል፤ ዕሴት፤ማንነት እና ወግ በተለያዩ ክዋኔዎች ባህላዊውን ከዘመነኛው ጋር ያሰናሰኑ ዝግጅቶች ቀርበዋል።
በዚህም በምግብ አዘገጃጀት፤በፋሽን ትርዒት፤ በሙዚቃ እና በሌሎች የጥበብ ስራዎች ባሀላዊው ከዘመናዊ ጋር በማሠናሠል ስራ የበረቱ ባለሞያዎች ስራዎቻቸውን አቅርበዋል።
የዝግጅቱ ዓላማም የሀበሻ መገለጫ የሆኑ አለባበሰ፣ምግብ ዝግጅት ፣ሙዚቃ እና የመሳሰሉትን በተለያዩ ሀገረኛ መድረኮች ብሎም በዓለም አቀፍ ደረጃ እንዲታወቁ ማድረግ እና እነዚህን ሁነቶች ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች ጎን ለጎን እራሳቸውንም እንዲያስተዋውቁ መደገፍ ነው።
📷 FastMereja





10 comments
እና ምን ይጠበስ
አረ በዛ በዚች ደሀ ሀገር እዬ ሁሉ አንባሳደር 😁😁😁
🍾🍷
ዳዊት ፅጌ ❤
ባንተ ሙዚቃ ውስጥ ፍቅርን እማውቃት ዘፈንክ አለ ስሜቱም አለ የኔ አንደኛ
ይገባዋል ❤
አልበም ሊለቅ መስሎኝ 😭
ዳዊቴ
Ere egnanis meche yemitaregun …
ሓበሻ ቢራ ታድያ ከባህል ጋር ምን የሚያያዝ ነገር አለው ቢራ ከቴክኖሎጂ ጋር የገባ መጠጥ ነውኮ 😏😏
ዘንድሮ ብራንድ አምባሳደር ያልሆነው እኔና #ደጀኔ ብቻ ነን… እንደቸገረን ቀረን እኮ ጎበዝ🙄