banner

ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ለ4 የልብ ሕሙማን ሕፃናት በነፃ ሕክምና ሊሰጥ ነው።

#FastMereja
ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል “ህጻናትን በልብ ህመም ከመሞት እንታደጋቸው” በሚል መሪ ቃል ሆስፒታሉ የተመሰረተበትን አንደኛ አመት እና የአዲስ ዓመትን በማስመልከት ለ3 ህጻናት ሙሉ በሙሉ ከክፍያ ነጻ የሆነ የልብ ቀዶ ህክምና ለመስጠት እንደተዘጋጀ ገለፀ።

ባለፈው አንድ ዓመት ብቻ ለ32 ሕፃናት የተሳካ የልብ ቀዶ ሕክምና በነፃ ማከናወኑን አቶ ብርሃን ተድላ የኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ባለቤትና ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተናግረዋል፣ ሕክምናው በገንዘብ ሲተመን 26 ሚልየን ብር እንደሚገመት ገልጸዋል።

በክብር እንግድነት የተገኘው አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ ታክመው የዳኑ ልጆች የነገ ሀገር ተረካቢ ናቸው ኢትዮ ኢስታንቡል ጠቅላላ ሆስፒታል ያከናወነው ሰብዓዊ ተግባር ሊበረታታ የሚገባ ነው ብሏል።

የሆስፒታሉን ጥረት ለማገዝና አጋርነታቸውን ለማሳየት አቶ ገበያው ታከለ 200 ሺ ብር፣ አቶ ጌቱ ገለቴ 500ሺ ብር ለግሰዋል።

አቶ ብርሃን ተድላ ለተደረገው ልግስና በልብ ሕሙማኑ ስም ምስጋና አቅርበዋል።





1 comment

Abebe Zeleke September 7, 2024 - 12:13 pm

የህፃናትን ህይወት ከመታደግ በላይ ወርቃማ ሥራ የለም። ፈጣሪ ብድራችሁ ያቆይ

Reply

Leave a Comment