banner

ቀድሞ መከላከል የሚቻሉ የጤና እክሎቸችን ባለማውቅ እና ቅድመ ምርመራ ባለ ማድረግ ሳቢያ የሚከሰቱ፤ እስከ የህይወት ህልፈት የሚ

ቀድሞ መከላከል የሚቻሉ የጤና እክሎቸችን ባለማውቅ እና ቅድመ ምርመራ ባለ ማድረግ ሳቢያ የሚከሰቱ፤ እስከ የህይወት ህልፈት የሚያደርሱ በሽታዎችን ለመከላከል ያለመ የነፃ ህክምና በአዲስ አበባ ተሰጠ።

የኩላሊትና የልብ ችግሮች ፣ ስኳር ፣ ደምግፊት፣ ካንሰርና መሰል ተላላፊ ያለሆኑ በሽታዎች ቀድሞ መከላከል እየተቻለ ነገር ግን ባለማወቅና ወደ ጤና ተቋማት ዘግይቶ በመምጣት ሳቢያ ከፈተኛ የሰው ህልፈትን እያስከተሉ ይገኛሉ።

እንደ አብነትም ባደጉ ሀገራት በቅደመ ምርመራ ሳቢያ የማህፀንና የጡት ካንሰር በሽታዎችን ገዳይነት ከ5 ከመቶ በታች ማድረስ ቢቻልም በኢትዮጵያ ግን በበሽታዎቹ ምክንያት የሚከሰት ሞት ምጣኔ አሁንም ከ50 ከመቶ በላይ ነው።

ኢንስቲዪዩት ኦፍ ሄልዚ ሜትሪክስ ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት ጋር በመተባበር ያሳተመው ጥናት እንደሚያሳየው እ ኤ አ በ2019 በአዲስ አበባ በበሽታዎች ምክንያት ከተከሰቱ ሞቶች ውስጥ 55 ከመቶ የሚሆኑት ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች የተመዘገበ ነው።

መሰል ነባራዊ ሁኔታዎችን መነሻ በማድረግ ፍቅረ ሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ማህበራዊ ሀላፊነትን መወጣት በሚል መርህ በትላንትናው እለት የነፃ የቅድመ ምርመራ ህክምና በመቶዎች ለሚቆጠሩ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች ሰጥቷል።

በሆስፒታሉ የጥራት ማሻሻያ እና ቁጥጥር ሀላፊ የሆኑት ሲ/ርቅድስትሀብተማርያም_ እንደተናገሩት ተላላፊ እና ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ቀድሞ መከላከል እና ከፍ ያለ ጉዳት ሳያስከትሉ መድረስ መቻል ዋነኛው በሽታዎቹን ለመቆጣጠር የሚያስችል መንገድ መሆኑን አንስተዋል።

ይሁን እንጂ በሀገራችን ያለው አነስተኛ ግንዛቤ ሰዎች ወደ ህክምና ተቋማት የሚመጡት በሽታው ከፍ ያለ ጉዳት ካስከተለባቸው ብቻ ነው የሚሉት ሲስተር ቅድስት በዚህም ሳቢያ የሚከሰቱ የህይወት ህልፈቶች ተበራክተዋል ብለዋል።

ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች የሚያስከትሉትን ሞት ለመቀነስ ባለመ ቅድመ ምርመራ አማካኝነት ፍቅረሰላም ሆስፒታል በትላንትናው እለት በሰጠው የነፃ አገልግሎት በተለምዶ ሀያት አደባባይ በሚባለው ስፈራ ከ350በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የቅድመ ምርመራ ህክምና መሰጠቱን ሲስተር ቅድስት ገልፀዋል።

የትላንቱ መርሀ ግብር ፍቀረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል አገልግልት መስጠት ከጀመረበት ካለፉት ስድስት ወራት ወዲህ ለሶስተኛ ጊዜ ያከናወነው ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል።

በጥቅሉ በ2016 ዓ.ም በሽዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች ህክምናው እንደተሰጠ አስታውሰው በመጭው አመትም ይህንኑ ማህበራዊ ሀላፊነት በሁለት ወር ለአንድ ጊዜ ለማከናወን ማቀዳቸውን አስገንዝበዋል።

ፍቅረሰላም አጠቃላይ ሆስፒታል ከ24 አመት በፊት በክልኒክ ደረጃ አገልግሎት መስጠት የጀመረ ሲሆን በአሁኑ ወቅትም ባስገነባው ባለ 9 ወለል ህንጻ አጠቃላይ የህክመና አገልገሎትን ከመስጠቱ ባሻገር ከ350 ዜጎች በላይ ቋሚ የስራ እደል መፍጠር ችሏል።





1 comment

Netsanet W Lakew September 9, 2024 - 5:30 pm

Social responsibility ማህበራዊ ሀላፊነት

Reply

Leave a Comment