banner

ሕብረት ኢንሹራንስ አዲሱን መለያ (ብራንድ) አስተዋወቀ

#FastMereja
ሕብረት ኢንሹራንስ ለሶስት አስርት አመታትን ሲጠቀምበት የነበረው የኩባንያውን መለያ በአዲስ መቀየሩን ዛሬ ጷጉሜ 4/2016 ዓ.ም በሸራተን አዲስ ሆቴል በተከናወነ ፕሮግራም አስተዋውቋል።

ኩባንያው በአሰራር ሂደቱ የተለያዩ ማዘመኛ ሂደቶችን እየተከተለ እና ዘመኑን የዋጀ አሰራርን እየተከተለ ለደንበኞቹ ይበልጡን ምቹ እየሆነ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን ከእነዚህ የአሰራር ማሻሻያዎች መካከል አንዱ እስካሁን ሲገለገልበት የቆየውን መለያ (ብራንድ) መቀየር እንደሚገኝበት ተነግሯል፣ ሙሉ የሎጎ እና የብራንዲንግ ስራውን አቶ ያየራድ ታደሰ እንደሰሩት ተገልጿል።

የሕብረት ኢንሹራንስ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ
አቶ ወንድወሰን ተሾመ “ኩባንያው ባለፉት ሰላሳ ዓመታት ሲገለገልበት የቆየውንና ብዙ ስኬት ያስመዘገበበትን ነባሩን ባለውለታ መለያ (ብራንድ) በክብር አሰናብቶ ዛሬ ላይ በእናንተ ፊት የሚመረቀውን አዲስ፣ ዘመናዊና ሕብረትን በቀላሉ የሚገልጽ አዲስ መለያ ወደሥራ በማስገባት ለሚቀጥሉት ሌላ አስርት ዓመታት ይዞት የሚጓዝ ይሆናል” ብለዋል፡፡

በ87 ባለራዕዮች በ25 ሚሊየን ብር መነሻ ካፒታልና በ8.073 ሚሊየን ብር የተከፈለ ካፒታል የተመሰረተው ህብረት ኢንሹራንስ ከተመሰረተበት ጊዜ አንስቶ በዘርፉ ውጤታማ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ ተነግሯል።

በሌላ በኩል የህብረት ኢንሹራን CEO (Chief excutive officer) ወ/ሮ መሰረት በዛብህ በዘንድሮው አመት የአፍሪካ ኢንሹራንስ ኩባንያዎች ምርጥ መሪዎች ምርጫ አሸናፊ ሆነዋል። ወ/ሮ መሰረት ይህን ውድድር ያሸነፉት ከመላው አፍሪካ ከተውጣጡ የኢንሹራንስ ኩባንያ መሪዎች ልቀው በመገኘታቸውም ነው።

በዕለቱም ወ/ሮ መሰረት ኢንሹራንሱን ብቻ ሳይሆን ሃገርን ወክለው ላደረጉት ውድድር እና ለአሸናፊነታቸውም ጭምር የእንኳን ደስ አላችሁ መልካም ምኞት ቀርቧል። በህብረት ኢንሹራንስ አዲስ መለያ ይፋ ማድረጊያ ስነ ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ገዢ አቶ ማሞ ምህረቱ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ምክትል ገዢ አቶ ሰለሞን ደስታን ጨምሮ በኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ የኢንሹራንስ ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና የኢንሹራንሱ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ተገኝተዋል።

የህብረት ኢንሹራንስ ፕሬዝደንት የ2024 የአፍሪካ የኢንሹራንስ ኩባንያዎች ምርጥ CEO አሸናፊ ሆነዋል።

📷 FastMereja





1 comment

Eliâs Abãynéh September 9, 2024 - 6:13 pm

ፓ! በጣም አሳስቦን ነበር እናመሰግናለን ✌️🤝😏

Reply

Leave a Comment