banner

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች የችግኝ ተከላ መረሃ ግብር አካሄደ

#FastMereja
። ዛሬ ጳጉሜ 4/2016 ዓ.ም በልደታ ከ/ከተማ አቦ ማዞርያ አካባቢ በሚገኘው ጊልዶ ዋሻ በተባለው ስፍራ የችግኝ ተከላ ፕሮግራም ተካሂዷል። በመረሃ ግብሩ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት የኤስ ኦ ኤስ መንደር ሰራተኞች ተገኘተው የአረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፏል።

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ የአለም አቀፉ ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች ፌዴሬሽን ብሄራዊ አባል የሆነ በህጻናት ደህንነትና ልማት ላይ አተኩሮ የሚሰራ ፖለቲካዊም ሃይማኖታዊም ያልሆነ የልማት ድርጅት ነው፡፡ ድርጅቱ ከተመሰረተበት ከ1974 ዓ.ም ጀምሮ በህጻናት፣ ቤተሰቦቻቸውና በማህበረሰብ ላይ እዎንታዊ ለውጦችን በማምጣት ላይ የሚገኝ የልማት አጋር ነው።

ኤስ ኦ ኤስ የህጻናት መንደሮች በኢትዮጵያ ላለፉት አምስት አስርት አመታት ያስመዘገባቸውን ታላላቅ ስኬቶች በመዘከር የተመሰረተበትን 50ኛ ዓመት በማከበር ሂደት ላይ ይገኛል፡፡

📷 FastMereja





Leave a Comment