banner

የንጉስ ቤተ መንግስት የመሰለው ፓራዳይዝ

#FastMereja

ጉዞ ተጀመረ 🚌
📍መነሻ አዲስ አበባ
📍መዳረሻ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን አርባምንጭ ከተማ
🏨 ማረፊያ በአረንጓዴው ፓራዳይዝ ሎጅ

የጋሞ ዞንን ለመጎብኘት ካሰቡ ዋና ከተማ አርባምንጭ ለመድረስ ሁለት አማራጭ አለ የየብስ እና እና የአየር ትራንስፖርት። የየብስ በመኪና ጉዞ ግማሽ ቀን ስለሚፈጅ በቡታጅራ እና በሐዋሳ መስመሮች አሉት። የአውሮፕላን በኢትዮጵያ አየር መንገድ በአንድ ሰዓት በረራ አርባምንጭ ይደርሳሉ።

ከኤርፖርት በምን ሆቴል ልሂድ ብለው በፍፁም አያስቡ ዛሬ የምናስቃኛችሁ የፓራዳይዝ ሎጅ ተሽከርካሪዎች እንኳን ደህና መጣችሁ ብለው ሻንጣችሁን ተቀብለው ተንከባክበው ወደ አረንጓዴው ወደ ተንጣለለው ግቢ፣ ገራሚ የተፈጥሮ እይታ ወዳለው የንጉስ ቤተ መንግስት ወደ መሰለው ፓራዳይዝ ሎጅ ያደርሶታል።

አሁን ፓራዳይዝ ደርሷል የትኛው ክፍል ማረፍ ይፈልጋሉ?

በፓራዳይዝ ሎጅ Normal, standard, VIP, VVIP የሆኑ በአጠቃላይ 99 የመኝታ ክፍሎች ይገኛሉ። በሎጁ አልጋ ይዘው ሲያርፉ የቡፌ ቁርስ፣ የገንዳ ዋና፣ ጂም፣ ስቲምና ሳውና በነፃ ያገኛሉ። ይመቾት!!

ስፋቱ አንድ መንደር የሆነው ፓራዳይዝ ሎጅ ብቻውን ውስጡ እየተጓዙ መጎብኘት ያለበት ቦታ ነው። አሻግረው ሲመለከቱ ከስር አርባዎቹን ምንጮች ቁልቁል የምታስተውሉበት ፤ ከእግዜር ድልድይ ጋር ፊት ለፊት የምትተያዩበት ፤ የአባያንና የጫሞ ሐይቆችን በግራና በቀኝ የምትቃኙበት በውብ ተፈጥሮ የታጀበ ስፍራ ነው።

እነዚህን በርቀት የምመለከታቸውን ስፍራዎች መመለክት አለብኝ ብለው ካሰቡ የትም መሄድ አይጠበቅም እህት ድርጅት የሆነው ኦሞ ቱር እና የመኪና ኪራይ ለጉዞ ለጉብኝት የሚሆኑ ዘመናዊ መኪኖችን አዘጋጅቶ ተንከባክቦ አስጎብኝቶ ይመልሶታል።

«Farm to table»
በፓራዳይዝ ሎጅ ምግብ ለማዘጋጀት የሚገዛው “ጨው” ነው። ሁሉም ምግብ ከእህት ድርጅት ኦሞቲክ ኦርጋኒክ ፋርም እና ከፓራዳይዝ ጓሮ ተቀጥፎ ወደ ኩሽና ይገባል። የእንስሳት ተዋፅኦ እና አትክልት፣ ፍራፍሬው ሁሉም ከራሳቸው እርሻ የሚቀርብ ነው።

📌 እዚህ ጋር ለመረጃ ስለ ኦሞቲክ ኦርጋኒክ ፋርም እቺን ለቅምሻ።
ኦሞቲክ ኦርጋኒክ ፋርም 34.5 ሄክታር ላይ ያረፈ የእርሻ መሬት ሲሆን በቀን በርካታ የጭነት መኪና ሙዝ ወደ ሶማሌ ላንድ ኤክስፖርት እንደሚደረግ ተነግሯል።

አርባምንጭ ከተማን በኦሞቲክ ቱር ሲጎበኙ አሁንም የኦሞቲክ ቢዝነስ ግሩፕ የሆነውን ሞቴል በአርባምንጭ ከተማ ያገኛሉ። ሞቴሉ የነዳጅ ማደያ እና ሁለገብ ህንፃ በአንድ ላይ የያዘ ሲሆን ህንፃው ግንባታ እየተከናወነ ይገኛል።

በአርባ ምንጭ ከተማ እና አከባቢዋ በርካታ የሚጎበኙ ስፍራዎች አሉ። አንድ ቀን ሁለት ቀን በቂ አይደለም። ጊዜ ወስደው ሰብሰብ ብለው በቤተሰብ፣ ከጓደኛ ጋር፣ ከወዳጅ ጋር፣ ከፍቅረኛ ጋር አሪፍ ጊዜ ያሳልፋሉ።

ፓራዳይዝ ሎጅ ተመልሰን በሬስቶራንቱ በውጭ በኩል አባያ እና ጫሞ ኃይቅ እየተመለከትን ንፁ አየር እየማግን ምግብ እየበላን ለመጨዋወት አመቺ ቦታ ነው። ፓራዳይዝ ሎጅ በ2000 ዓ.ም ተቋቋመ፣ 99 የመኝታ ክፍሎት ሲኖሩት የመሰብሰቢያ አዳራሾች፣ ጂም፣ የመዋኛ ገንዳ፣ ስፓ፣ ማሳጅ፣ የህፃናት መጫወቻ ስፍራ፣ እንዲሁም በውስጡ ሰናይት ፓርክን የያዘ ግዘፍ ሎጅ ነው።

ጉብኝት አጠናቀው ወደ መጡበት መመለስ ሲፈልጉ ፓራዳይዝ ሎጅ ከኤርፖርት ተንከባክቦ እንዳመጣችሁ በሰላም ግቡ በማለት ተንከባክቦ ወደ ኤርፖርት ይመልሳል።

ሰላም ሁኑ 🙏
ተመልሰን እንመጣለን።





6 comments

ሩቅ ምስራቅ September 30, 2024 - 2:10 pm

ኧረ ተው ግን ስራ ፈልጉልኝ ተው እኔ ወንድማችሁ ያለ እድሜዬ አረጀሁ በማሪያም 🙏

Reply
Fitsum Amdemichael September 30, 2024 - 2:12 pm

በሰላም ተመላለሱ

Reply
Mõĥãmmêď Ĩbňū Ŝēmmëř September 30, 2024 - 2:15 pm

ቤቴ ነው።✌

Reply
Beri Love Sime September 30, 2024 - 2:18 pm

Betachin nw

Reply
Huda Ahmed September 30, 2024 - 2:19 pm

አይቸው 3ቀን አድሬ ተዝናንቼበት አለሁ እንደተባለውም ቆንጆ ቦታ ነው ሄዳችሁ ጎብኙት😎

Reply
Ëýé Ëvåñ Mäń September 30, 2024 - 2:21 pm

ጋሞ my city #አርባምንጭ ምን አይነት ውቤት ነው የሰጠሽ ፈጣሪ 😍😍😍😍

Reply

Leave a Comment