0
#FastMereja
ዛሬ ከምሽቱ ሁለት ሰአት ገደማ አያት አካባቢ እንዲሁም አጎራባች ስፍራዎች ላይ አስደንጋጭ የመሬት መንቀጥቀጥ መከሠቱን መሠረት ሚድያ ዘግቧል።
መሠረት ሚድያ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጂኦ-ፊዚክስ፣ ስፔስ ሳይንስና አስትሮኖሚ ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር ዶ/ር ኤልያስ ሌዊን ያነጋገረ ሲሆን በትክክል የመሬት መንቀጥቀጥ እንደነበር አረጋግጠዋል።
“ከሰሞኑ ከፈንታሌ ጀምሮ እስከ አዲስ አበባ የተሰማ የመሬት መንቀጥቀጥ ነበር። ይህ የዛሬ ምሽቱ ከሱ ጋር የተያያዘ ይሁን ወይስ ሌላ አዲስ የሚለውን ገና እናጣራለን” በማለት ለመሰረት ሚዲያ ምላሽ ሰጥቷል።

10 comments
እሬቻ የጣኦት አምልኮ ነው ስንል በምክንያት ነው ገና እሳት ያዘንቡብናል😕😕😕
ገና ብዙ ነገር ይመጣብናል የሰው ልጅ ደም እንደጎርፍ እየፈሰሰ የሰው ልጆች ስንባል በአሁኑ ጊዜ ከፈጣሪ ህግ ወጥተናል እና እሱ አይነ ልቦናችንን ያብራልን😭
የዋቃ ጉራቻ ጣኦት ገና እሳት ያዘንቡብናል
እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቃችሁ እንደበደላችን ሳይሆን እንደ ምህረቱ ይቅር ይበለን በዚሁ ይመልሰው 🙏
የድንግል ማርያም ልጅ ኢትዮጲያን አደራ ጠብቃት
ጭሮ (አሰበ ተፈሪ) ከተማ 2:10 ሳዓት ላይ ተንቀጥቅጧል
እኛን ምስኪኖቹን ትቶ ወደ ቤተመንግሥቱ ያድርግልን 🙏
አብይ ወንበዴው በጦርነት አልችል ሲለን በመሬት መንቀጥቀጥ ህዝባችንን ለመጨረስ የብልጽግና ሴራ እንደሆነ መረጃ አለን። የፋኖ ቃለ አቀባይ😀😃😄
ደብረዘይት አዳማ አዋሽ 7 አዲስ አበባ ጨምሮ 4ከተሞች ላይ በተመሳሳይ ሰዓት ተከስቷል
i was around 6kilo but nothing happened