banner

ሀይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ እና ሀብኪዶ ከ አዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የሰልጣኞች ምርቃትን ምክንያት

ሀይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ እና ሀብኪዶ ከ አዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የሰልጣኞች ምርቃትን ምክንያት በማድረግ በመቄዶንያ ለ አንድ ሺ አረጋውያን የምሳ ማብላት ዝግጅት እንደሚያካሂድዱ ገለፁ

ሀይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ እና ሀብኪዶ በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በመቄዶንያ ተማሪዎቹን እሁድ ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም የሚያስመርቅ ሲሆን ምርቃቱንም ምክንያት በማድረግ አንድ ሺ አረጋውያንን ከ አዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር በመቄዶንያ አንድ ሺ አረጋውያን የምሳ ማብላት ፕሮግራም ለማዘጋጀት የቅድመ ዝግጅት ስራ እየሠራ መሆኑን ዛሬ መስከረም 28 ቀን 2017 ዓ.ም በአራት ኪሎ ወ.ክ.ማ.በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫው ተገልጿል።

ሀይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ እና ሀብኪዶ የተለያዮ የሀገር ውስጥ እና የውጪ ሽልማቶችን ያገኘ የቴኳንዶ ክለብ ሲሆን ጥቅምት 3 ከሁለት መቶ በላይ ተማሪዎቹን ለማስመረቅ በዝግጅት ላይ ሲሆን ሀይሌ ቤስት በ 2018 በክረምትና እና በበጋ ሲያሰለጥናቸው የቆዩትን ሰልጣኞች በመቄዶንያ ግቢ ውስጥ ያስመርቃል በዚህም ዝግጅት ለ 1,000 ሰው የምሳ ማብላት ፕሮግራም ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል።

ሀይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ ማሰልጠኛ ለዚህ በጎ አላማ ተጋባዥ ክለቦችን እና ድርጅቶችን በማቀናጀት ለበጎ ስራው በሰፊው እየተንቀሳቀሰ ሲሆን አንድ ትኬት ለአንድ ወገን በማለት ትኬቶችን እየሽጠ ሌሎች እንዲሳተፋ እያደረገ ይገኛል። እንዲሁም በእለቱ ህንደኬ የኪነ ጥበብ ቡድን፣ መንታ ሚዲያ፣ ማንኪራ ዲኮር፣ ፍካት ኤቨንት እና ዲኮር፣ መቄዶንያ በጋራ ለዚህ በጎ ስራ ይሳፋሉ ተብሏል።

በምርቃት ዝግጅቱ ላይ የአዲስ አበባ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ኃላፊ ጥላሁን ዋሲሁን፣ማስተር በፍቃዱ ታደሰ የወርልድ ቴኳንዶ አሰልጣኞች፣ የመቄዶንያ ዋና ስራ አስኪያጅ ቢንያም በለጠ እና የክብር እንግዳዎች በተገኙበት ጥቅምት 3 ቀን 2017 ዓ.ም በመቄዶንያ ግቢ ውስጥ ይደረጋል፡፡

ሀይሌ ቤስት ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት ክለብ በኢትዮጵያ 2002 ዓ.ም የተቋቋመ የቴኳንዶ ክለብ ሲሆን ለአስራ አምስት አመታት የቴኳንዶ ተማሪዎችን በማሰልጠን ቆይቷል አሁን ላይ በአራት ቅርንጫፎች በሰሚት ፣ ጎሮ፣ የካ አባዱ እና ቦሌ አራብሳ በማስፋት እያሰለጠነ የሚገኝ ክለብ ነው።





Leave a Comment