banner

የኮንታ ነዋሪዎች በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ይቅርታ ይጠይቅ ሲሉ ቅሬታቸውን አሰሙ።

#FastMereja 📍 ኮንታ ማለት የጥጋብ ምድር ናት። የእህል ልመና እና እርዳታ የማታውቅ ምድር ናት። ኮንታ የፍቅር ምድር ናት ዛሬ ላይ አማራ፣ ኦሮሞ፣ ወላይታ፣ ሀድያ፣ ከፋ፣ ዳውሮና እና ሌሎችም ብሔሮች ተዋደው እና ተፋቅረው የሚኖሩባት ሀገር ናት ሲሉ ነዋሪዎቹ ለፋስት መረጃ ባደረሱት ቅሬታ ተመልክተናል።

እንግዳ አክባሪዎች ነን። “ኮንታ ትገባላችሁ” ያለው ሰውዬው ሁኔታ ብቻውን ለእንግዶች ምን ያህል ክብር እንዳለን አመላካች ነው ብለዋል።

ለአንድ ቀን ኮንታን አይቼ እመለሳለሁ ብሎ የመጣ ሰው ሳምንታትን የሚቆይበት ምድር ናት። እንጂ ተገብቶ የማይወጣባት አይደለችም ብለዋል።

የዚህን ሰውዬ አነጋገርና እንግዳ አቀባበል ሁኔታውን እንደመነሻ በመውሰድ በማህበራዊ ሚዲያዎች የተለያዩ ቀልዶች ስቀለዱ ዝም ብለን አይተናል።

አሁን ከማህበራዊ ሚዲያ አልፎ ወደ ዋናው ሚዲያ መጥቷል ያሉት ነዋሪዎቹ በኢቢኤስ ቴሌቪዥን እሁድን በኢቢኤስ ፕሮግራም ላይ «በዚህ እንዳትሄዱ ኮንታ ትገባላችሁ» እያሉ ሲያፌዙ አይተናል ያሉት ኮንታዎች ”እንደሱ አትደውይ ኮንታ ትገብያለሽ ” እያሉ በሚዲያ ያለ አግባብ ቃሉን መጠቀማቸው ቅሬታ አሳድሮብናል ብለዋል።

በተጨማሪም በኢቢኤስ ቴሌቪዥን በተላለፈ ማስታወቂያ ላይ “ኮንታ ትገባላችሁ” የሚለው በድርጅት ማስታወቂያ ላይ በድምፅ ተሰርቶ ኮንታ መግባትን እንደመጥፎ ነገር በማድረግ ማስታወቂያ በጣቢያ ላይ ሲተላለፍ ተመልክተናል ብለዋል።

ሁሉም የኮንታ ተወላጆች እና የኢትዮጵያ ዜጎች የዚህን አይነት ሚዲያ ተግባር መቃወም አለብን ሲሉ የኮንታ ነዋሪዎች ለፋስት መረጃ ባደረሱት የቅሬታ መልዕክት ተመልክተናል።




6 comments

Bruçk Tâm October 15, 2024 - 11:53 am

ኮንታ ሲዖል መስሎኝ

Reply
Wendimu Tafesse October 15, 2024 - 11:53 am

አው ቅር ተሰኝተናል

Reply
Dige A Wagiso October 15, 2024 - 11:53 am

የኮንታ ተወላጅ ነኝ።

EBS ይቅርታ ይጠይቀን👍

Reply
Melik Brhanu October 15, 2024 - 11:53 am

😂😂😂😂

Reply
ጥቁር ሀበሻዊ October 15, 2024 - 11:53 am

እኔ አሁን ላይ ኮንታ መግባት ፈልጋለው ውሰዱኝ

Reply
Fu Ad October 15, 2024 - 11:53 am

አይ እማማ Ethiopia ስራ ፈትሽ በዛ

Reply

Leave a Comment