banner

ምርጥ ተፅእኖ ፈጣሪ ስራዎች 10 ሚሊዮን ብር ሊሸለሙ ነው።

#FastMereja I ምርጥ ተፅእኖ ፈጣሪ ስራዎች (Best Influencer Work prize) የተሰኘ ሽልማት ሊካሄድ ነው።

የBIW prize አላማው በኢትዮጵያ ውስጥ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት በተለየ መንገድ ጥረት ለሚያደርጉ እና በህዝቡ መካከል ሰላማዊ አብሮነትን ለማጎልበት ለሚተጉ በስራቸውም ለሌሎች አርአያ ለመሆን የቻሉ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን ማበረታታት እና ስራቸውንም ማገዝ እንደሆነ ዛሬ ጥቅምት 11/2017 ዓ.ም በአዳማ በተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ተገልጿል።

ከመላው ኢትዮጵያ የሚመረጡ በኢኮኖሚ ሽልማት ዘርፍ እና ለሰላም ሽልማት ዘርፍ የBIW prize አሸናፊዎች በአንቴከስ ጨርቃጨርቅ ኃ.የተ.የግ.ማህበር እና ፉድ ኤይድ ፕላስ የምግባረ ሰናይ ድርጅት እውቅና እና ለስራቸው ማጠናከርያ ይሆን ዘንድ ታህሳስ 17 ቀን 2017 በአፍሪካ ህብረት የስብሰባ ማእከል ከፍተኛ የመንግስት አካላት እና የክብር እንግዶች በተገኙበት ለሁለቱም ለእያንዳዳቸው 10 ሚሊዮን ብር ለአሸናፊዎች የገንዘብ ሽልማት ይበረከትላቸዋል ተብሏል።





Leave a Comment