#FastMereja I ከተማዋ በወቅቱ ይህን ህግ ያወጣችው የትዳር ፍቺን ለመከላከል በሚል እንደነበር ተገልጿል።
ከተማዋ በ1907 ዝሙት መፈጸምን የሚከለክል ህግ ያወጣች ሲሆን ይህን ህግ ተላልፎ የተገኘ ሰው የሶስት ወር እስር ያስቀጣም ነበር።
ይሁንና ከተማዋ ይህን የዝሙት ህግ ከወንጀልነት የሰረዘች ሲሆን ምክንያቱ ደግሞ ህጉ ወቅቱን አይመጥንም በሚል ነው።
የኒውዮርክ ከንቲባ ካቲ ሆቹል ህጉን በይፋ ሶስት ወር ቅጣትን የሚጥለውን ህግ መሰረዙን ተናግረዋል ። ከንቲባው አክለውም ህጉ ወቅቱን ያልጠበቀ እና ያረጀ እንደሆነም ጠቅሰዋል።
ከትዳር ውጪ የሚደረግ ወሲብን ለመከልከል በሚል የተዘጋጀው ይህ ህግ አጥፊዎችን ለመያዝ አስቸጋሪ ነው መባሉ ለህጉ መሻር ሌላኛው ምክንያት እንደሆነም ተገልጿል።
ህጉ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ በ12 ሰዎች ላይ የዝሙት ወንጀል ክስ የተመሰረተ ሲሆን አምስት ሰዎች ብቻ ተቀጥተዋልም ተብሏል።
ለመጨረሻ ጊዜም በዚህ ወንጀል ክስ የተመሰረተው በ2010 ዓመት ላይ ሲሆን ክሱ በስምምነት ተቋርጧል።
ኒዮርክ ይህን አነጋጋሪ ህግ በ1960 ላይ ለመሰረዝ አስባ የነበረ ቢሆንም በወቅቱ የህጉ መሰረዝ የትዳር ፍቺን ያባብሳል በሚል ፖለቲከኞች ባሰሙት ተቃውሞ ምክንያት ሳይሰረዝ ቀርቷል።
በቴዎድሮስ መኩሪያ

6 comments
እውነት ነው ጊዜውን አይመጥንም
ቴክኖሎጂ እዚ በደረሰበት ዘመን
ሁሉም ነዋሪዋ የየ3 ወር እስ re ኛ ሆነው ነው ሚቀሩት😭😭
ሴት ልጅ ላንተ ብላ እራሷን ካጠፋች ትወድካለች ማለት ነዉ ቶሎ አግባት
They’re 101% Alright time is for technology’s 😃
ባትስርዝሽ ትተው ነበር እንዴ😁
አጀብ 😭😭😭
እግዚአብሔርን የማትሰማ፣ ይህቺ ክፉ ትውልድ የሞላባት ዓለም😢