0
የኢትዮጵያ ባህልና እሴት እንደዚሁም የፋሽን ኢንዱስትሪውን የፋሽን ሽግግር ለማሳየት ያለመ ትርኢት የፊታችን አርብ ህዳር 27/2017 ዓ.ም.ይደረጋል።
በዚህ የፋሽን ትርኢት በዳይመንድ የተሰሩ ሁለት አልባሳት በትርኢቱ ላይ እንደሚቀርቡ ነው የተነገረው።
አርብ በሚደረገው የባህልና ዘመናዊ የፋሽን ትርኢት ከ15 በላይ ሞዴሎች ስራዎቻቸውን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል።
የኢትዮጵያ የፋሽን ቴክኖሎጂ ሽግግር ይታይበታል በተባለው በዚህ ትርኢት ላይ አምባሳደሮች ሞዴሎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ይገኙበታል ተብሏል።
የዚህ ትርኢት አዘጋጅ የሆነችው ዲዛይነር እና ሞዴል ሜላት ሚካኤል የኢትዮጵያን ባህላዊ አለባበስ ከዘመናዊው ፋሽን ጋር ጋር ለማስተሳሰር ትልቅ እድል ይፈጥራል ብላለች።
በዚህ የፋሽን ትርኢት ላይ ድምጻዊት ዊሀ የሙዚቃ ስራዎቿን ታቀርባለች ተብሏል።
ባህላዊውን ከዘመናዊው ጋር ያስተሳሰረው የፋሽን ትርኢት የፊታችን አርብ በታህሣስ 4 ቀን 2017 ዓ.ም.በሀያት ሪጀንሲ ሆቴል እንደሚደረግ አዘጋጆቹ ተናግረዋል።




