banner

3 ሚሊዮን ብር ለህክምና ያስፈልጋል

የሰአሊ ብሩክ የሺጥላ የስእል አውደ ርእይ የፊታችን ህዳር 26 በሸራተን አዲስ ሆቴል ለእይታ ይበቃል የስእል አውደ ርእዩ አላማ ሰአሊ ብሩክ የሺጥላ በስዊድን ሃገር ለሚያደርገው የጉልበት ንቅለ ተከላ ህክምና የሚውል ሲሆን ሰአሊው ገንዘብ በእርዳታ ከማሰባሰብ ይልቅ በራሱ የእጅ ስራዎች የጥበብ ውጤቶች ለመታከም ታስቦ የተሰናዳ አውደ ርእይ ነው።

የእውደ ርእዩ ስያሜ ነፃነት ሲሆን ከስእል እይታው በተጨማሪም የተለያዩ ጨረታዌች ይከናወናሉ ተብሏል። በመርህ ግብረ ላይ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ፣ባለሃብቶች እና የጥበብ ሰዎች ይገኛሉ ተብሎ ይታሰባል።

ሰአሊ ብሩክ የሺጥላ ስዊድን ሃገር ለሚያደርገው የጉልበት ንቅለ ተከላ 3 ሚሊዬን ብር ያስፈልጋል።
Organizers ራኬብ ሐብቴና ኤደን ገብረህይወት




Leave a Comment