0
#FastMereja I አንቴክስ ያዘጋጀው የመጀመሪያው የሰላም ዘርፍ እና የኢኮኖሚ ዘርፍ ሽልማት ዛሬ ታህሳስ 17/2017 ዓም በአፍሪካ ህብረት ተካሂዷል።
🏆 የሰላም ዘርፍ አሸናፊ የጋሞ አባቶች
🏆 የኢኮኖሚ ዘርፍ አሸናፊ ኢ/ር ቢጃይ ናይከር
ለሁለቱም አሸናፊዎች የ10 ሚሊዮን ብር ሽልማት ተሰጥቷል።
ኢ/ር ቢጃይ ናይከር በተወካይ በኩል ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ ሽልማቱን ተጨማሪ 20 ሚሊዮን ብር በመጨመር ፌስቡክ ላይ ከዚህ በፊት እንደሚያደርገው እንደሚሸልም ገልጿል።
የBIW prize አላማውን በኢትዮጵያ ውስጥ ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት በተለየ መንገድ ጥረት ለሚያደርጉ እና በህዝቡ መካከል ሰላማዊ አብሮነትን ለማጎልበት ለሚተጉ በስራቸውም ለሌሎች አርአያ ለመሆን የቻሉ ግለሰቦችን እና ድርጅቶችን ማበረታታት እና ስራቸውንም ማገዝ ነው ።
አንቴክስ ጨርቃጨርቅ ኃ.የተ.የግ.ማ. በኦሮሚያ ክልል አዳማ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን በአዳማ ኢንደስትርያል ፖርክ ከ10 በላይ ሼዶች ሲኖሩት ለ4500 ሰራተኞች የስራ እድል የፈጠረ ድርጅት ነው።





3 comments
እና እኛ የመረጥነው ምን እንጠቀማለን ???
ታሪኩ ጋንኪሲ ነው የህዝብ አሸናፊ ። ማፈርያዎች!!!!
ወያኔን ድምጥማጡን ያጠፋው የ “ድምፃችን ይሰማ” ትውልድ ነኝ🔥🔥🔥