0
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ አቶ ያብባል አዲስ፥ የአሮጌ መኪና ባለቤቶች መኪናቸውን በፍጥነት መቀየር ካልቻሉ በለሙ የኮሊደር መንገዶች ላይ እንዳይንቀሳቀሱ ክልከላ ሊደረግባቸው ይችላል ብለዋል።
አሮጌ መኪናዎች የአገልግሎት ዕድሜ ገደብ ፀድቆ ወደስራ ሊገባ ይገባል ያሉት ኃላፊው አሁን አግልግሎት እየሰጡ ያሉ የአሮጌ መኪና ባለቤቶች ፈጥነው መቀየር እንዳለባቸው እንደተገለጸላቸው ተናግረዋል።
መኪናዎቹ በካርቦን ልቀት፤ በትራፊክ መጨናነቅና በተገልጋዮች ምቾት አለመስጠት እንቅፋት እየሆኑ ነው ተብሏል።
የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ከተሽከርካሪ ባለንብረቶችና ከአስመጪዎች ጋር በመሆን የብድር አገልግሎት እንዲያገኙና መኪኖች ከቀረጥ ነፃ እንዲገቡ ድጋፍ እንደሚሰጥ ሰምተናል ሲል አራዳ ሬዲዮ ነው የዘገበው።
10 comments
አሮጊት እና ሽማግሌስ😂
ሌላ የትችት እርስ
ፈርዶበታል መንግስት 😋😊
አለባበስ አይተዉ ብቻ መንገድ እንዳያስቀይሩን
ገና በሙሉ ልብስ ካልዘነጣቹ ከቤት እንዳትወጡ እንባለለን 🙄 አይ ፀሀዩ መንግስታችን 😏 ተደበሩብን
ብቻ አካል ጉዳተኞን ከቤት እንዳትወጡ እንዳይባል 😢
የትኛው አለም ላይ ነው ሰውዬው የሚኖረው ከህልሙ ተነስቶ እንዲህ መጫወቻ ያድርገን አይ እማማ ኢትዮጵያ😏😏😏
ገና ህዝቡም እንደሚያግዱት ይጠበቃል
እውነት ለመናገር እኔ የምኖረው ከሀገር ውጪ ነው የ 1990 እንዲሁም ከዛ በታች ያሉ መኪናዎች እራሱ ይነዳሉ ስለዚህ ቢታሰብበት መልካም ነው
እድሜ ይስጠን እንጂ ገና ብዙ …………….
ላዳ ጉድሽ ፈላ ! 🤣